"ሀገር ወዳድነትና የሃገረ መንግስት ግንባታ ሂደት" በሚል ርዕሰ ጉዳይ ከአዲስ አበባ ከተማ ለተወጣጡ ወጣቶች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል ።
"ያለፉትን ችግሮች አንስቶ በመውቀስ ብቻ ጊዜ ማባከን ሳይሆን ሁላችንም በአገር ወዳድነት ስሜት ለአገራችን እንደ አቅማችን መልካም ነገር በመሥራት ያለችና የምትኖር ኢትዮጵያን ማስቀጠል ይገባናል"
አቶ ስፋዬ ጫኔ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ም/ቢሮ ሃላፊ
ታህሳስ 15/2017 (አዲስ አበባ)
****
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የሰላም እሴት ግንባታና የሀይማኖት ጉዳዮች ዘርፍ "ሀገር ወዳድነትና የሃገረ መንግስት ግንባታ ሂደት" በሚል ርዕሰ ጉዳይ ከአዲስ አበባ ከተማ ለተወጣጡ ወጣቶች
የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል ።
በመድረኩ ላይ በመገኘት መልዕክት ያስተላለፉት አቶ ተስፋዬ ጫኔ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ም/ሀላፊ እንደ አገርም ወጣቶችን ያላሳተፈ ሃገራዊ ጉዳይ ፤አይሰመርምና የሀገር ግንባታ ውስጥ ትልቁ ሚና ስላላቸው ከነጠላ ትርክት በመውጣት የጋራና አሰባሳቢ የሆነ ትርክትን ማስቀደም ይገባል ብለዋል።
አገራችን ኢትዮጵያ የተለያዩ የአስተዳደር ችግሮች የነበሩባት ቢሆንም ቀደም ብላ አገርን የመሰረተች ናት፤ዛሬ ደግሞ ያለፉትን ችግሮች አንስቶ በመውቀስ ብቻ ጊዜ ማባከን ሳይሆን ሁላችንም በአገር ወዳድነት ስሜት ለአገራችን እንደ አቅማችን መልካም ነገር በስራት ያለችና የምትኖር ኢትዮጵያን ማስቀጠል ይገባናል ሲሉ ተናግረዋል።
የግንዛቤ ማስጨበጫ ሰነዱን ያቀረቡት አቶ ኤልያስ ቀጄላ አገር ወዳድነት ማለት ከጥቅምና ከስልጣን ያለፈ ለሃገሩ ስሜት ያለውና ለሃገሩ ማንኛውም መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ የሆነ ነው ብለዋል።
በማብራሪያቸውም የአገር ወዳድነት ፋይዳ፣ የኢትዮጵያ አገራዊ ማንነት፣የአርበኝነት አይነቶችና ባህሪያቱ፣ እና ስለመሳሰሉት.. አብራርተዋል።