ከጥምቀት በዓል አከባበር የቅድመ ዝግጅት ጋር ተያይዞ ክትትልና ድጋፍ የሚያደርግ ቡድን ተቋቋመ።
ከጥምቀት በዓል አከባበር የቅድመ ዝግጅት ጋር ተያይዞ ክትትልና ድጋፍ የሚያደርግ ቡድን ተቋቋመ።
ታህሳስ 16/2017ዓ.ም (አዲስ አበባ)
****
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የሰላም ዕሴት ግንባታና የሃይማኖት ጉዳዮች ዘርፍ ከጥምቀት በዓል አከባበር ጋር ተያይዞ እየተደረጉ ያሉ ዝግጅቶችን በተመለከተ በ11ዱም ክ/ከተማ ክትትልና ድጋፍ የሚያደርግ የክትትልና ድጋፍ ቡድን ተቋቋሟል።
የቢሮው ም/ልሃላፊ አቶ ተስፋዬ ጫኔ ለቡድኑ ኦረንቴሽንና ሥምሪት አቅጣጫ በሰጡበት ወቅት እንደተናገሩት፡-ይህ ክትትልና ድጋፍ በዋናነት የሚያተኩረው፣በተሰጡት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎች መሰረት ከሃይማኖት ተቋማትና አድባራት፣ታቦታት የሚያርፉበት የጥምቀት ባህር ቦታ፣የስጋት አይነቶችና ቦታዎችን በመለየት፣የሃይማኖትተቋማት፤
ከፀጥታ አካላትና ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ጋር ያላቸው ቅንጅታዊ አሰራር ምንእንደሚመስል ለማየትና ችግሮችም ካሉ ከሃይማኖት ተቋማትና ጉባኤ ጋር የሚፈቱበትን ሁኔታ ለማመቻቸት እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
ድጋፍና ክትትል የሚያደርገው ቡድን በአራት ተከፍሎ የሚሰማራ ሲሆን ለ3 ቀናት በየክፍለ ከተማና ወረዳዎች መስክ ላይ እንደሚቆይ ለማወቅ ተችሏል፡፡