ከተማ አቀፍ የሰላም ኮንፈረንሱ ባለ አራት ነጥብ...

image description
- recent news   

ከተማ አቀፍ የሰላም ኮንፈረንሱ ባለ አራት ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት ተጠናቀቀ

ከተማ አቀፍ የሰላም ኮንፈረንሱ ባለ አራት ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት ተጠናቀቀ

             ታህሳስ 17/ 2017 (አዲስ አበባ)

                           ******

በመርሐ ግብሩ ላይ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ሲሆኑ የለዉጡ መንግስት ሀገራችንን መምራት ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ የከተማችንን ልማትና ሰላም በመጠበቅ ውስጥ በርካታ ድሎችን ማስመዝገብ ተችሏል ያሉት ሀላፊዋ ሰላማችንን ለማደፍረስ የሚጥሩ አንዳንድ አካላት እንዳሉ የሚታወቅ ሲሆን በአንፃሩ ደግሞ በቅርቡ የሰላም ጥሪውን በመቀበል ወደ ህብረተሰቡ የተቀላቀሉ መኖራቸውን በመግለፅ አሁንም ቀሪ አካላት የሰላም ጥሪውን መቀበሉ ለአገራችን ሁለንተናዊ ሰላምና ዕድገት የሚበጅ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ህብረተሰቡን የሰላም ባለቤት ለማድረግና በተፈጠሩት አደረጃጀቶች የአካባቢንም ብሎም የሀገርን ሰላም ለማስጠበቅ የልማት ስራዎች በተቀመጠላቸው ልክ ለማጠናቀቅ ሰላም መከበር ይኖርበታል፡፡ በቀጣይም በከተማችን ላይ በርካታ የአደባባይ በዓላት የሚከበሩ በመሆኑ ሁሉም የበኩሉን ድርሻ ሊወጣ ይገባል ብለዋል።

በመድረኩ ላይ በመገኘት ለተሳታፊዎች መልዕክት ያስተላለፍት አቶ አብርሃም ታደሰ የአዲስ አበባ ከተማ የብልግና ፖርቲ ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ በበኩላቸው የከተማዋን ሰላም ለማስጠበቅ ህብረተሰቡ ለሰላም በከፈለው ዋጋ የተመዘገቡ ዉጤቶችን ዘላቂ ማድረግ ይገባል በማለት ተናግረዋል ።

ለኮንፈረንሱ ተሳታፊዎች ከኢፌድሪ የሰላም ሚኒስቴር ዶ/ር አወቀ አጥናፉ የሰላም ግንባታ ዋና ሥራ አስፈፃሚ "ሀገር ወዳድነትና የሰላም ግንባታ" በሚል መሪ ቃል ሰነድ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡ 

በመጨረሻም ኮንፈረንሱ ባለ አራት ነጥብ የአቋም መግለጫ በማዉጣት ተጠናቋል፡፡