በመዲናዋ ሕገ-ወጥ ንግድን ለመቆጣጠር
በመዲናዋ ሕገ-ወጥ ንግድን ለመቆጣጠር የተናበበ እና የተቀናጀ ስራ በመሰራቱ ውጤት በመገኘቱ የህግ የበላይነት ለማስፈን ቁጥጥሩ አሁንም ሊጠናከር ይገባል።
የአዲስ አበባ ሰላም እና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ሀላፊ
ታህሳስ 16/2017 ዓ.ም
በመዲናዋ ሕገ ወጥ ንግድን ለመቆጣጠር የተናበበ እና የተቀናጀ ስራ በመሰራቱ ውጤት መገኘቱን የአዲስ አበባ የሰላም እና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ እና የህግ የበላይነትና ቁጥጥር ንኡስ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወይዘሮ ሊዲያ ግርማ ገልጸዋል።
ይህንን ውጤት ለማስቀጠልም ቅንጅታዊ አሰራርን በማጠናከር የሕግ የበላይነትን ማስፈን እንደሚገባም ጠቁመዋል።
በገበያ ማዕከላት ከደላላ ነጻ የሆነ የግብይት ስርዓት እንዲሰፋ ጥብቅ ቁጥጥር ማድረግ ላይ በትኩረት መስራት እንደሚገባም ገልጸዋል።
ከተሰጣቸው ንግድ ፈቃድ ውጪ በሕገ ወጥ ስራ ላይ የተሰማሩ, ያለደረሰኝ ግብይት የሚፈጽሙና የሕዝቡን ባህልና ስነ ልቦና የማይመጥኑ የምሽት ቤቶችን ጨምሮ በሌሎች መሰል ህገ ወጥ ተግባራት ላይ በጥናት የተመሰረተ ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰድ መመሪያ ሰጥተዋል።
ያለ ንግድ ፈቃድ የሚሰሩ ፣ ባልታደሰ የንግድ ፈቃድ የሚሰሩ እና ያለደረሰኝ ግብይት የሚፈጽሙ ነጋዴዎች ላይ ጥብቅ ቁጥጥር በማድረግ አሁንም በቅንጅት መስራት እንደሚገባ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅተናግረዋል።
በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ 172 ደረጃቸውን የጠበቁ የእሁድ ገበያ ማዕከላት ለጤናማ የንግድ ስርዓት መስፈን ከፍተኛ አበርክቶ እያደረጉ መሆኑም ተገልጿል።