ቢሮው አዲስ ሠልጣኝ የሰላም ሰራዊት አባላትን ለሚያሰለጥኑ የፖሊስ አመራሮችና አባሎች ስለ ሥልጠናው ገለፃ አደረገ።
ቢሮው አዲስ ሠልጣኝ የሰላም ሰራዊት አባላትን ለሚያሰለጥኑ የፖሊስ አመራሮችና አባሎች ስለ ሥልጠናው ገለፃ አደረገ።
ታህሳስ 16/2017 (አዲስ አበባ )
****
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የህዝብ የአደረጃጀት ዘርፍ አዲስ ሥጣኝ የሰላም ሰራዊት አባላት በንድፈ ሀሳብና በተግባር ስልጠና ለሚሰጡ የፖሊስ አመራሮችና አባላት ስለ ሥልጠናው ገለፃ አድርጓል።
የውይይት መድረኩን በንግግር ያስጀመሩት የቢሮው ሃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ እንደተናገሩት አንደኛ ዙር የነባር ሰላም ሰራዊት አመራሮች ሁለንተናዊ አቅም ማጎልበቻ ስልጠና ስለሰጣችሁ በቢሮውና በራሳቸው ስም አመስግነው የጸጥታ ስራ በጸጥታ መዋቀር ብቻ መስራት የሚቻል ስላልሆነ ቢሮው ማህበረሰቡን በማሳተፍ የከተማዋን ሰላም ለማረጋገጥ አገር ተረካቢ ወጣቶችን ያሳተፈ 22 ሺ ለሚሆኑ አዲስ ሠልጣኝ የሰላም ሰራዊት አባላት የንድፈ ሃሳብና የአካል ብቃት ስልጠና ሰጥቶ ለማስ
መረቅ ዝግጅቱን የጨረሰ መሆኑን ጠቁመዋል።
በውይይቱ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ሃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ፣የቢሮው ም/ቢሮ ሃላፊ አቶ ሚደክሳ ከበደ፣የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ኮሚሽን የማህብረተሰብ አቀፍ ፖሊስ አግልግሎት ሃላፊ ረዳት ኮሚሽነር አይናለም በየነን ጨምሮ ሌሎች የፖሊስ አመራሮችና አባሎች ተሳትፈዋል።