ነባር የሰላም ሰራዊት ምርቃት
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የንድፈ ሀሳብና የተግባር ማነቃቂያ ስልጠና ያጠናቀቁ ነባር የሰላም ሰራዊት የብሎክ አመራሮችን አስመረቀ።
ታህሳስ 18/2017 ዓ.ም (አዲስ አበባ)
****
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ በ1ኛ ዙር 4992 የሚሆኑ በንድፈ ሐሳብና በወታደራዊ የመስክ ሲያሰለጥናቸው የነበሩ ነባር የሰላም ስራዊት የብሎክ አመራሮች በዛሬ ዕለት በአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ ሰባት 15 ሜዳ ተብሎ በሚጠራ ሥፍራ ላይ እያስመርቋል።
በመርሃ-ግብሩ መጀመሪያ ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ፣ ከተማችን አዲስ አበባ የሀገራችን ርዕስ ከተማ፣የዓለም አቀፍ ዲፕሎማቶች መቀመጫ ከመሆኗ ጋር ተያይዞ በርካታ ኢኮኖሚ የሚንቀሳቀስባትና መጠን ደረጃውን የሚመጥን የሰላምና ፀጥታ ተቋም በማስፈለጉ የተቋቋመው ቢሯችን ሌሎች ህግ አስከባሪ ተቋማትን በማቀናጀት በማስተባበርና በመምራት የከተማውን ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ ሌት ተቀን እየተጋ ይገኛል ካሉ በኃላ ቢሮው ይህንን ዓላማውን ለማሳካት በፈጠረው አደረጃጀት ውስጥ በንቃት በመሳተፍ የከተማችንን ሰላም በማስፈናችሁ ምስጋና ይገባችኋል ብለዋል።
ክብርት የቢሮ ኃላፊዋ አክለውም ያለምንም የስነ ስርዓት ችግር ይሄ ስልጠና ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ ድረስ አስተዋጽኦ ላበረከቱና በተሻለ ብቃት የሰላምና ፀጥታውን ስራ ለመስራት ስልጠናው ያስፈልገናል ብለው በጥሩ ሥነ-ሥርዓት ተከታትለው ያጠናቀቁ የሰላም ስራዊት የብሎክ አመራሮችን አመሰግናለሁ፡፡ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል፡፡
በመጨረሻም በቀጣይም ከፊታችን የሚከበር የአደባባይ በዓል፤ጥምቀት በሰላም ተከብሮ እንዲጠናቀቅ በወሰዳችሁት ስልጠና መሰረት ሰላም የመጠበቅ ተልዕኳችሁን እንድትወጡ ከአደራ ጭምር አሳስባለሁ ብለዋል።
የአዲስ አባባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ም/ል ሃላፊ ቢሮ ኃላፊ የሆኑት አቶ ሚደቅሳ ከበደ በዚህን ወቅት እንደታገሩት የሰላም ስራዊት አደረጃጀት ከሁሉ በላይ የአገር ፍቅርና አንድነት ላይ በፅኑ አቋም ያለው አደረጃጀት፣በወል ትርክት የሚያምን የሰላም አንድነት ማስተባበሪያና ማሰሪያ ገመድ፤ የዕድገትና የልማት አርበኛ ነው ሲሉ ገልጸዋል።
በመጨረሻም ስልጠናውን ያጠናቀቁ ሰልጣኞች ከክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ እና የክብር እንግዶች፣የምስክር ወረቀትና የዋንጫ ሽልማትተበርክቶላችዋል።