የዘንድሮዉን የጥምቀት በዓል አከባበር አስመልክቶ ውይይት ተደረገ፡፡
የዘንድሮዉን የጥምቀት በዓል አከባበር አስመልክቶ ውይይት ተደረገ፡፡
ታህሳስ 18/2017 ዓ.ም (አዲስ አበባ)
****
የአዲስ አበባ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ፤ የአዲስ አበባ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ እና የአዲስ አበባ ሀገር ስብከት ዘንድሮ የሚከበረውን ጥምቀተ ባህር የታቦታትት ማደሪያ ቦታዎች አከባቢ የሚስተዋሉ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችል ውይይት ተደርጓል፡፡
የጥምቀት በዓል በተባበሩት መንግስታት የሳይንስና የባህል ማዕከል በዓለም በማይዳሰሱ ቅርሶች የተመዘገበ የዓለም ቅርስ እንደመሆኑ መጠን በዓሉን ለማክበር ከተለያዩ የዓለም ጫፎች በርካታ ቱሪስቶች የሚሳተፉ በትና ዓለማቀፍ ሚዲያዎች የአየር ሽፋን ለመስጠት የሚታደሙበት ስለሆነ እንደ ሃገር የሚሰጡት ኢኮኖሚያዊና ዲፕሎማሲያዊ ጥቅሞች ከፍተኛ መሆኑ በውይይቱ ወቅት ተጠቅሷል፡፡
በመሆኑም በዘንድሮ ዓመት የሚከበረው የጥምቀት በዓል ቅድመ ዝግጅት ለማድረግ፤ የታቦታት ማደሪያ አከባቢ የሚታዩ የቦታ እጥረቶችና በዓሉ በሰላም እንዳይከበር የፀጥታ ስጋት ምልክቶችን ቀድሞ በመለየት ለችግሮች መፍትሄ ለመሻት የተፈጠረ የውይይት መድረክ መሆኑ ታውቋል፡፡
በውይይት መድረኩ ላይ የመልካም አስተዳደር ችግሮችና በዓሉን በሰላም ለማክበር እንደ እንቅፋትወይንም ፀጥታ ስጋት ሊወሰዱ የሚችሉ ጥቃቅን ጉዳዮች በአስቸኳይ እንዲፈቱ በክብርትየቢሮ ኃላፊዋ አቅጣጫ የተቀመጠ ሲሆን በዓሉ በሰላም ተከብሮ እንዲያልፍ ሁሉም የበኩሉን ሚና መወጣት አለበትም ብለዋል፡፡