ቢሮው የጥምቀት በዓል በሰላምና በአብሮነት ተከብሮ እንዲውል ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችና አደረጃጀቶች ጋር ውይይት አደረገ።
ቢሮው የጥምቀት በዓል በሰላምና በአብሮነት ተከብሮ እንዲውል ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችና አደረጃጀቶች ጋር ውይይት አደረገ።
ጥር 05/ 2017 ዓ.ም (አዲስ አበባ)
********
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የ2017 ዓ/ም የጥምቀት በዓልን አስመልክቶ በዓሉን በሰላም፣በአብሮነትና በወንድማማችነት በጋራ ለማክበር እንዲቻል ምክክር አድርገዋል።
ዛሬ ሙሉ ቀን በተካሄደዉ በዚህ መድረክ ላይ ጠዋት ከማዕከል እስከ ወረዳ ከሚገኙ የሃይማኖት ጉባኤ አባቶች ከሰዓት በኃላ ደግሞ ከሰላም ሠራዊት፣ከበጎ ፈቃዳኞች፣ከወጣቶችና ሴቶች ተወካዮች ጋር የተደረገ ውይይት ነው።
በውይይት መድረኩ ላይም የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ም/ል ቢሮ ሀላፊ አቶ ተስፋዬ ጫኔ የውይይቱ ዓላማ በዋናነት በከተ
ማችን በየደረጃው ያሉ የባለድርሻ አካላት በዓሉ በሰላም ተከብሮ እንዲጠናቀቅና፣ለሀገራችን የጥምቀት በዓል የመቻቻል ፣ የአብሮነት እና የወንድማማችነት ተምሳሌት ሆኖ የሚታይበት በዓል ስለሆነ ባለድርሻ አካላት የየ ድርሻቸውን ኃላፊነት ወስደው በዓሉ በሰላም እንዲከበር ማድረግ አለባቸው ብለዋል።
በመጨረሻም ለውይይት መነሻ በሆነው ሰነድ ላይ ሰፊ ውይይትና መግባባት ላይ ተደርሶ ውይይቱ ተቋጭቷል።
በመድረኩ ላይም የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ም/ል ሀላፊ አቶ ተስፋዬ ጫኔ፣ከ11ዱም ክፍለ ከተማ የተወጣጡ
ከሃይማኖት ተቋማት አባቶች፣ከወጣቶች፣
ከሴቶች፣ከሠላምሠራዊትና እንዲሁም የማዕከል እና የክ/ከተማ የዘርፉ ባለሙያዎች ተገኝተዋል።