የጥምቀት በዓል ቅድመ ዝግጅት
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ የጥምቀት በዓል አከባበርን በማሰመልከት ከአዲስ አበባ ሴቶች ማህበር ተወካዮች ጋር ውይይት አካሄደ።
ጥር 06/ 2017 ዓ.ም (አዲስ አበባ)
******
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ ም/ል ቢሮ ኃላፊ አቶ ሚዴክሳ ከበደ እንደተናገሩት ሴቶች አከባቢ
ያችሁን በንቃት የምትጠብቁ የከተማችን የሰላም አምባሳደሮች ናችሁና አሁንም ከፊታችን በድም
ቀትየሚከበረው የጥምቀት በዓል በሰላም እንዲከበር በተለመደው ንቃትና መነሳሳት መጠበቅ ይኖርባችኃል ብለዋል።
የቢሮው የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ፍሬሕይወት በለጠ የመወያያ ሰነድ ያቀረቡ ሲሆን፣በገለጻቸው ወቅት ይህ መድረክ ዋና ዓላማ የ2017 የጥምቀት በዓል አከባበር ያለምንም ፀጥታ ችግር ተከብሮ እንዲጠናቀቅ ከሴቶች ማህበር ተወካዮች ጋር በጋራ በመወያየት ወደ ስራ እንዲገቡ ለማድረግ ነው ብለዋል።
በአከባቢያቸው የፀጥታ ስጋትን መለየትመቆጣ
ጠር፣በዓሉ ከሚከበርበት አከባቢ የተለያዩ ተቀጣጣይ ነገሮችን ማራቅ፣ፀጉረ ልውጦችን እንቅስቃሴ መከታተል፣ወንጀሎችንና የወንጀል ድርጊቶችን በጥብቅ መከታተል፣የመረጃቅብሎ
ሹን ወቅታዊና ፈጣን ማድረግ፣የኮሪደር ልማቱ እንዳይበላሽ የመንገድ አጠቃቀምን ማሳየት እንደሚገባ ተናግረዋል።
የከተማችን ሴቶች የሰላምን አስቀድመው የሚሰሩ ትጉ ሲሆኑ አሁንም ለበዓሉን ሰላም መከበር ሚናቸው ከፍ ያለ ነው ያሉት የአዲስ አበባ ከተማ የሴቶች ማህበር ፕሬዘዳንት ወ/ሮ እናት ዓለም እንዳለ ሁሉም እሴቶች የተሰጣቸ
ውን ብሎክ በመጠበቅና መረጃዎችን በመለዋ
ወጥ ኃለፊነታቸውን መወጣት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።
በመድረኩ ላይ የቢሮው ም/ል ኃላፊ አቶሚደክሳ ከበደ የአዲስ አበባ ከተማ የሴቶች ፕሬዘዳንት ወ/ሮ እናትዓለም እንዳለ፣ም/ል ፕሬዘዳንት ወ/ሮ አፀደ አበነ እና የዘርፉ ዳይሬክተር ባለሙያዎች የክ/ከተማ አስተባባሪዎች ተገኝተዋል።