የቀጠለ ዜና.

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

የቀጠለ ዜና.

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ የጥምቀት በዓል በሰላም ተከብሮ እንዲያልፍ ከአዲስ አበባነዋሪዎች፣የተለያዩ የፀጥታ አጋዥኃይሎችና ደረጃጀቶች ጋር ውይይት አደረገ።

ጥር 07/2017 ዓ.ም (አዲስ አበባ)

****

የቢሮው የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ የከተራና የጥምቀት በዓል በሰላም ተከብሮ እንዲያልፍ ከአዲስ አበባ ነዋሪዎች፣ከታዋቂና ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦችና እንዲሁም ከተለያዩ የፀጥታ አጋዥ ኃይሎችና ደረጃጀቶች ጋር ውይይት አድርጓል።

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ ም/ል ቢሮ ኃላፊ አቶ ሚደክሳ ከበደ በመክፈቻ ንግግራቸው የከተራና የጥምቀት በዓል ፍፁም ሰላማዊ ሆኖ፣ዕሴቶቱንና ሃይማኖታዊ ትውፊቱን ጠብቆ እንዲከበር ሁሉም ድርሻውን ሊወጣ ይገባል ብለዋል።

በጠዋትና በከሰዓት በኃላ የውይይት መድረክ ላይ ከአዲስ አበባ ነዋሪዎች፣ከተራአስከባ

ሪዎች፣ጫኝና አውራጅ፣ከፓርኪንግ ከፀጥታ ኮሚቴና የሰላም ምክር ቤት አባላት የተውጣጣ ከ2200 በላይ ሰው የተሳተፈበት እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል።

በከተማው ውስጥ ከሚገኙ 119 የወረዳ የሕዝብ አደረጃጀቶች ጋር በመጪው ከተራና

የጥምቀት በዓልን አስመልክቶ ውይይት መደረጉንጠቅሰው፣የዛሬው መድረክ በየደረጃው ሲደረግ የነበረው ውይይት መቋጯና ስምሪት መስጫ ነው ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ም/ል ኃላፊ አቶ ሚደክሳ በመክፈቻ ንግግራቸው ገልጸዋል።

የመወያያ ሰነዱን ያቀረቡ የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ የስልጠና ባለሙያ የሆኑት አቶ አቶ አብርሀም እንግዳወርቅና አቶ ውድነህ አቢ ሲሆን፣በገለጻቸው ወቅት የዚህ መድረክ ዋና ዓላማ ከከተራ እስከ ጥምቀት በዓል አከባበር ከፀጥታና ከባለድርሻ አካላት ከደንብ ማስከ

በር ጋር በቅንጅት በመስራት በዓሉ በሰላም ተከብሮ እንዲጠናቀቅና የህብረተሰቡን ደህንነት ለመጠበቅ ነው ብለዋል።

ሁለቱም የውይይት መድረኮች የ2017 ዓ/ም የጥምቀት በዓል አከባበር ታሪካዊ ዳራ እና አሁናዊ ሁኔተዎችን አስመልክቶ ለውይይት መነሻ የሆነ ሰነድ በዘርፉ ባለሙያዎች ቀርቦ ውይይት ከተደረገ በኃላ የአቋም መግለጫ በማውጣት ተጠናቋል።

በውይይት መድረኩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ም/ል ቢሮ ሀላፊ አቶ ሚደክሳ ከበደ፣ከ11ዱም ክ/ከተማየተወጣጡ ነዋሪዎች የህብረተሰብ ክፍሎች አባ ገዳዎችና አደስንቄዎች የማዕከልና የክ/ከተሞች አስተባባሪዎችና ባለሙያዎች ተገኝተዋል።