መጪው የከተራና የጥምቀት በዓል ሰላማዊ ሆኖ እን...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

መጪው የከተራና የጥምቀት በዓል ሰላማዊ ሆኖ እንዲከበር የሰላም ሰራዊቱ አከባቢውን በንቃት እየጠበቀ ነው።

መጪው የከተራና የጥምቀት በዓል ሰላማዊ ሆኖ እንዲከበር የሰላም ሰራዊቱ አከባቢውን በንቃት እየጠበቀ ነው።

ላፍቶ፣ ጥር 7/2017:- በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ መጪው የከተራና የጥምቀት በዓል ሰላማዊ ሆኖ እንዲከበር የሰላም ሰራዊቱ አከባቢውን በንቃት እየጠበቀ ይገኛል።

በዛሬው ዕለት የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ጫኔ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ምክትል ኃላፊ ኮማንደር አህመድ መሀመድ ጨምሮ ሌሎች ከክፍለ ከተማ አመራሮች በጋራ በመሆን የሰላም ሰራዊቱን የፀጥታ ስምሪት ተዘዋውረው በመመልከት አበረታተዋል።

መጪው የከተራና የጥምቀት በዓል ሀይማኖታዊ እሴቱን ጠብቆ በሰላም እንዲከበር የሰላም ሰራዊቱ ከደንብና ከፖሊስ ጋር በቅንጅትና በትብብር መስራት እንደሚገባው በሰምሪት መርሃ ግብሩ ተመላክቷል።

ይህ በዓል በአደባባይ የሚከበር በመሆኑ ፀረ ሰላም ኃይሎች የእኩይ አላማና ፍላጎታቸው ማሳኪያ እንዳያደርጉት ከወትሮው የተለየ ጥበቃ ማድረግና በዓሉ በሰላም እንዲያልፍ የሰላም ሰራዊቱ የበኩሉን ኃላፊነት መወጣት እንዳለበት ተገልጿል።