ከሰላም ሰራዊት አመራሮችና አባላት ጋር የተደረገ ውይይት
የሰላም ሰራዊት አባላት እንደ ቀድሞ ሁሉ በዓላት በሰላም እንዲከበሩ ሀላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባ ተገለጸ።
ጥር 8/ 2017 ዓ/ም(አዲስ አበባ )
****
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ መጭው የከተራና የጥምቀት በዓል በሰላም ለማክበር እንዲቻል ከሁሉም ክ/ከተማ ከተወጣጡ ከሰላም ሰራዊት አመራሮችና አባላት ጋር ውይይት አድርጓል።
በውይይቱ ላይ በመገኝት ንግግር ያደረጉት ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ሀላፊ እንዳሉት የ ከተማችን አዲስ አበባ ላይ ከፀጥታ ኃይሎች ጋር እጅና ጓንት ሆነን በመሥራታችን አሁን ላይ አስተማማኝ ሰላም ከማምጣትም በላይ ከተማዋ የሰላም ተምሳሌት እንድትሆንም አስችሏታል ብለዋል።
ክብርት ሀላፊዋ አያይዘውም የተጀመሩ የከተማ የመልካም አስተዳደር፣ የኮሪደር ልማት ስራዎች በተቀመጠላቸው ጊዜ ሊጠናቀቅ የቻለው አስተማማኝ ሰላም በመኖሩ ነው ብለዋል።
የሰላም ሰራዊቱ አሁንም የሰላም የጸጥታው ስራ የጀርባ አጥንት በመሆኑ ሰላሙን ለማጽናት በዓላት በሰላም እንዲከበሩ ፣የወንጀል ድርጊች እንዳይፈጠሩ የጠላት እኩይ ተግባራት እንዳይሳኩ የሰላም ሰራዊት አባላት እንደ ቀድሞ ሁሉ ሀላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባም ሀላፊዋ አሳስበዋል ።
በዓሉ በርካታ የውጭ ሀገር ቱሪስቶችና የህብረተሰብ ክፍሎች የሚታደሙበት እንደመሆኑ መጠን ወንድማማችነትና ህብረብሔራዊነታችንን ለአለም አጉልተን የምናሳይበት መሆን መቻል ስላለበት የሰላም ሰራዊት አባላት ከሌሎች የጸጥታ አካላትና የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ዋልታና ማገር በመሆን ሃላፊነታችሁን እንድትወጡ አደራ አላለው በማለት አሳስበዋል ።
የመወያያ ሰነዱን ያቀረቡ የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ ዳይሬክተር ወ/ሮ ፍሬሕይወት በለጠ ሲሆኑ፣በገለጻቸው ወቅት የዚህ መድረክ ዋና ዓላማ ከከተራ እስከ ጥምቀት በዓል አከባበር ከፀጥታና ከባለድርሻ አካላት ከደንብ ማስከ
በር ጋር በቅንጅት በመስራት በዓሉ በሰላም ተከብሮ እንዲጠናቀቅና የህብረተሰቡን ደህንነት ለመጠበቅ ነው ብለዋል።