የሰላም ሰራዊት ምርቃት

image description
- recent news   

የሰላም ሰራዊት ምርቃት

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ  የ2017 ዓ.ም 2ኛው ዙር ዕጩ የሠላም ሠራዊት አባላትን በአበበ ቢቂላ መታሰቢያ ስታድየም አስመረቀ።

              ጥር 9/2017 ዓ.ም

በምረቃ መርሃግብሩ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ ከህዝብ የተወጣጣና የከተማችን ዋነኛ የሰላም ዘብ የሆነው የሰላም ሰራዊታችንን አሰልጥኖ እንዲመረቅ ማደረግ ከፀጥታ አጠባበቅ ስራ ግን ለጎን በህዝቦች መካከል መቀራረብን፣በጋራ አጀንዳ ላይ መግባባትና የህዝቦችን ትስስር በመፍጠር አንድነትና ወንድማማችነትን ማጠናከር ዓላማው ያደረገ ተግባር  ነው ብለዋል።

የከተማችን ስላምና ፀጥታ ለማስተዳደር ፣ የደንብ ጥሰቶችን ለመከላልና ለመቆጣጠር ከህዝብ የተወጣጡ ጠንካራ የሰላም ስራዊት አደረጃጀት በመፍጠር የህዝብ የሰላም ባለቤትነት ማጠናከር ተገቢ ነው ያሉት ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ የዛሬው የፀጥታ አጋዥ ሃይል የንድፈ ሀሳብ እና ወታደራዊ ስልጠና ምረቃም አደረጃጀቱን በሰው ሀይል የማጠናከር ስራችን ማሳያ ሲሆን በዚህ የስልጠና ሂደት የሰላም ሰራዊት አባላት ጠንካራ  የህግ አስከባሪ ሃይል እንዲሆን ይጠበቃል ብለዋል።

የዛሬው ተመራቂዎች  በቀጣይም የፀጥታ አጠባበቅ ስራ ላይ የሚሰጣችሁን ኃላፊነት በተገቢው እንድትወጡ አደራ ጭምር እያሳሰብኩ ለዚህ ውጤትና ስልጠናው በወጣለት መርሀ ግብር እንዲጠናቀቅ ሌት ተቀን ጥረት ላደረጉ አመራሮች፣የፖሊስ ኃሊፊዎች፣አሰልጣኞች፣ድጋፍ ሰጪ ባለሙያዎች፣በየደረጃው የፀጥታ አሰተዳደር ተቋማት አመራርና ባልደረቦችን አመስግነዋል።

የቢሮ ም/ል  ሀላፊ አቶ ሚደክሳ ከበደ በበኩላቸዉ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የ2017ዓ.ም 11,000 ዕጩ አዲስ የሰላም ስራዊት አባላት ለተከታታይ 15 ቀናት በንድፈ ሐሳብ ፣ የመስክ ወታደራዊ፣ የአካላት ብቃት  ወንጀልን መከላከል፣የስጋት ቦታው ልየታ እና አካላዊ ፍተሻ፣በዕውቀት በክህሎት በአመለካከት እና በአካላዊ ብቃት ዝግጁ ማድረግ መቻሉን ተናግረዋል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮምሽን ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ክቡር ኮምሽነር ጌቱ አርጋ በበኩላቸው 
በከተማችን አዲስ አበባ  በ4 ዓመቱ የለውጥ አመታት ውስጥ ጠላቶቻችን ሁከት ለመፍጠር ያላደረጉት ጥረት የለም። ነገር ግን የፀጥታ መዋቅሩ፣የሰላም ሠራዊትና ሕብረተሰቡ ባደረጉት ያላሰለሰ ጥረት ሊከሽፍ ችሏል። ለዚህም ሁሉንም ተቋማት አመስግናለሁ ብለዋል።

አዛዡ ጨምረውም የዛሬ ተመራቂዎች መጪው የጥምቀት በዓል ያለምንም የፀጥታ ችግር በሠላም ተከብሮ እንዲያልፍ ከፀጥታ ተቋማት ጋር በመቀናጀት የበኩላችሁን አስተዋፅኦ እንድታበረክቱ አሳስባለሁ ብለዋል።

በምረቃ መርሃ ግብሩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ፣የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮምሽን ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ክቡር ኮምሽነር ጌቱ አርጋ፣ከፍተኛ የመንግስት ኃላፊዎች የማዕከል ም/ል ቢሮ ሀላፊዎች እና የክ/ከተሞች ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ኃላፊዎች ተገኝተዋል።