የ6ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ እና የደንብ ማስከበር ባለስልጣን የ2017
በጀት አመት የ6ወራት ዕቅድ አፈጻጸማቸዉን ገመገሙ።
ጥር 15/2017 ዓ.ም (አዲስ አበባ)
*****
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ እና የደንብ ማስከበር ባለስልጣን የ2017 በጀት አመት የ6ወራት ዕቅድ አፈጻጸማቸውን ከማዕከል እስከ ወረዳ የሚገኙ የሁለቱም ተቋማት በየደረጃው ያሉ አመራሮች በተገኙበት ገምግመዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ በጋራ ግምገማ መድረኩ መክፈቻ ላይ እንደተናገሩት ባለፈው በከተማችን የተከበሩት የከተራና የጥምቀት በዓላት አንድነታችንን፣ አብሮነታችንና ብሎም የሀገራችንን ገፅታ ከፍ አድርገን ያሳየንበት በመሆኑ በዓሉ ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መንገድ ተከብሮ እንዲጠናቀቅ አስተዋፅኦ ያበረከቱትን ሁሉ አመስግነዋል።
ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ አክለውም የዛሬው መድረክ በዕቅዱ መሠረት በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን ጠቅሰው፣በተለይም ከፀጥታ አካላት ጋር ያለው የመረጃ ፍስት፣ከባለድርሻ አካላት ጋር የነበረው ቅንጅታዊ አሠራር የከተማችንን ሰላም ማስጠበቅ መቻሉን፣ የከባድ ወንጀል ክስተት ምጣኔን 48% እንዲቀንስ ማድረግ መቻሉ፣የከተማው ኢኮኖሚ እንቅስቃሴ እያደገ መምጣቱን፣ህብረተሰቡ ከፀጥታ መዋቅሮች ጎን በመቆም የሰላም ባለቤት እንዲሆኑ በርካታ ስራዎች መሰራታ ቸውን፣በሁለት ዙር ከ22.000 በላይ የሰላም ሠራዊት አባላትን በመመልመል፣ማሰልጠንና ማሰማራት መቻሉም ሌላው ስኬት ነው ብለዋል።
የሁለቱም ተቋማት የስድስት ወራት ሪፖርት ከወረዳ ጀምሮ በየደረጃው ተገምግሞ የመጣ ቢሆንም በማዕከል ደረጃም ቀርቦ ጥልቅ ግምገማዊ ውይይት ተደርጎበታል።
የአዲስ አበባ ከተማ የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ሥራ አሥኪያጅ ሻለቃ ዘርይሁን ተፈራ በበኩላቸው በሁለቱም ተቋማት ከማዕከል እስከ ወረዳ ያለው ቅንጅታዊ አሰራር ይበል የሚያሰኝና ተጠናክሮ መቀጠል ያለበት ነው ያሉት ሻለቃ ዘርይሁን ተፈራ ሕብረተሰቡን የሰላም ባለቤት ማድረግ፣ብልሹ አሰራሮችና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን መፍታት ቀዳሚ ሥራችን ሆኖ መቀጠል ይኖርበታል ብለዋል።
ክብርት ሊዲያ በግምገማው ማጠቃለያ ላይም ባስቀመጡት አቅጣጫ፣በቀጣይ ሌብነትና ብልሹ አሰራርን አምርሮ መታገል፣ተቋምን በሰው ኃይል፣በቴክኖሎጂና በአሰራር ማጠናከር፣
በቴክኖሎጂ የተደገፈ አገልግሎት ማሳደግ፣
የጥቆማ ስርዓት መዘርጋትመተግበር፣የጫኝና አውራጅ ማህበራትን መከታተልና መቆጣጠር፣
የሠላም ሠራዊት ቁጥርን በቀሪ ወራትማሳደግ፣
የማህበረሰብ አቀፍ ውይይቶች አጠናክሮ ማስቀጠል ወዘተ..ያስፈልጋል ብለዋል።
በግምገማ መድረኩ ላይ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ፣ሻለቃ ዘርይሁን ተፈራ የአዲስ አበባ ከተማ የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ሥራ አሥኪያጅ ና እንዲሁም ከማዕከል እስከ ወረዳ የሚገኙ አመራሮች ተገኝተዋል።