ሁለተኛ ዙር የሰላም ሰራዊት ስልጠና እና ያለፈው የጥምቀት በዓል ቅንጅታዊ ሥራ አፈፃፀም ተገመገመ።
የ2017 ዓ.ም በጀት ዓመት ሁለተኛ ዙር የሰላም ሰራዊት ስልጠና እና ያለፈው የጥምቀት በዓል ቅንጅታዊ ሥራ አፈፃፀም ተገመገመ።
ጥር 20/ 2017 ዓ/ም(አዲስ አበባ )
****
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ በ2017ዓ.ም በጀት አመት ሁለተኛ ዙር የሰላም ሰራዊት የንድፈ ሀሳብና የመስክ ወታደራዊ ስልጠና እንዲሁም ያለፈውን የጥምቀት በዓል ቅንጅታዊ ስራ አፈፃፀምን ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት የግንዛቤ ዲቪዚዮን ጋር ገምግሟል።
በግምገማ መድረኩ ላይ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ም/ሀላፊ አቶ ሚደቅሳ ከበደ እንደተናገሩት ሁለተኛው ዙር የሰላም ሰራዊት ከምልመላ እሰከ ስልጠና መጠናቀቅ ድረስ እንዲሁም ያለፉት የከተራና የጥምቀት በዓላት ፍጹም ሰላማዊ በሆነ መልኩ እንዲጠናቀቅ ጉልበታችሁን ሳትሰስቱ በማገልገል ወንጀልን ለመከላከል ተጨማሪ አቅም ሊሆኑን የሚችሉ አዲስ የሰላም ሰራዊት አባላትን በማሰልጠን ከፍተኛ አስተዋፅኦ በማድረጋቸው አመስግነዋል።
አቶ ሚደክሳ አክለውም ያለፉት በዓላት እንደ ሌላው ግዜ ብቻ ያልነበረ ፍጹም ሰላማዊነት የታየበት፤ የጠላት ሴራ ከማህበረሰቡ ጋር በቅንጅት በመስራት እንዲከሽፍ የተደረገበትና የሀገር ከፍታ ጉልቶ የወጣበት እንደነበር ጠቅሰው የአደባባይ በዓላት ሰላማዊነት ከግዜ ወደ ግዜ እየተሻሻሉ የመጡት ማህበረሰቡን በማወያየት የሰላም ባለቤት እንዲሆኑ በመሰራቱ መሆኑን ጠቅሰው ነገር ግን ያለፈው ሰላማዊነት ለቀጣዩ ጊዜ ዋስትና ስለማይሰጥ ምንግዜም ዝግጁ ሆነን መገኘት ይኖርብናል ብለዋል።
ለውይይቱ መነሻ የሆነውን ሰነድ አቶ አብርሃም እንግዳወርቅ የቢሮው የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ ቡድን መሪ ያቀረቡ ሲሆን በበዓላቱና በሥልጠናዉ ጠንካራ አፈፃፀም የታየባቸውን ተግባራት በማስቀጠል የታዩ ክፍተቶችን ማረም በትኩረት ሰቶ መስራት የይገባል ብለዋል።
የግምገማ መድረኩ ተሳታፊችም በቀጣይ ለስተከከሉና የጋራ ተግባራትን የሚያጠነክሩ ናቸው ያሉትን ሃሳቦችና ጥያቆዎች አንስተዉ ከመድረኩ ምላሽና ማብራሪያ እንዲሁም በአቶ ሚደክሳ ከበደ የቢሮው ም/ኃላፊ አቅጣጫ ተሰጥቶበታል፡፡
ኮማንደር መቅደስ ተስፋዬ የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አግልግሎት የህብረተሰብ ግንዛቤ ዲቪዝዮን ኃላፊ በበኩላቸው በዓላት በሰላም እንዲከበሩ የሰላም ሰራዊት አባላት ስልጠናም በሰላም እንዲጠናቀቅ የሰራናቸው ስራዎች ውጤታማ ናቸው፡፡የጸጥታ ስራ በወቅታዊ ሁኔታ ላይ ብቻ የተንተራሰ ሳይሆን ሁልግዜም በበለጠ በመስራት የተሻለ ውጤት በስራችን ላይ ማስመዝገብ ይገባናል ሲሉ ተደምጠዋል።