የ6ወር እቅድ አፈጻጸም ግምገማ ከማዕከል ሰራተኞች ጋር
የቢሮው የማዕከል አመራሮች፣ዳይሬክተሮችና ባለሙያዎች የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ የ6ወራት እቅድ አፈጻጸም ገመገመ ።
ጥር 22/2017ዓ.ም ( አዲስ አበባ )
******
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የማዕከል አመራሮች፣ዳይሬክተሮችና ባለሙያዎች የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ የ6ወራት የእቅድ አፈጻጸም ገምግሟል።
መድረኩን የመሩት የቢሮው ጽ/ቤት ሃላፊ ሲሆኑ መጀመሪያ እቅዱን ሲናቅድ የከተማውን የፀጥታ ሁኔታ መሰረታዊ በማድረግ እና ተናበን በማቀዳችን፣ስራ ላይ ተረባርበን በመስራታችን እና ከተቋማት ጋር በቅንጅት በመስራታችን ውጤታማ ሆነናል ካሉ በኋላ የአደባባይ በዓላት ያለምንም የፀጥታ ችግር በሰላም ተከብረው ማለፋቸው ቢሮው የአፈጻጸም አቅሙ እየጨመረ መሆኑ ማሳያ ነው ሲሉ ገልጸዋል።
መድረኩ ላይ የቢሮው ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ተሻለ አክሊሉ የግምገማውን አስፈላጊነት ሲገልፁ በመጀመሪያ 6ወራት ውስጥ ችገሮችም ካሉ በመወያየት ፈተን ፣ ያሉት ክፍተቶች በቀሪው ስድስት ወራት ውስጥ አሻሻለን እንድንሰራ ነው ብለዋል።
የስድስት ወራት ሪፖርት ያቀረቡት የቢሮው አቶ ማስረሻ ሃብቴ ሲሆኑ የበጀት አጠቃቀም አሰራር እና ውጤታማነቱን ማሻሻል፣ የሰው ሃብት አስተዳደር አሰራር ውጤታማነት መሻሻል፣ የአብይ ግቦች ዋና ዋና ተግባራት፣ ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ ያሉት ጠንካራ ጎኖችና ክፍተቶች ዝርዝር ማብራርያ ሰጥተዋል።
ካሉት ጠንካራ ጎኖች መካከልም የህብረተሰብ ተኮር ውይይት በማድረግ የህብረተሰቡ ተሳትፎ ማጎልበት፣ የቅንጅት ስራዎች ከተለያዩ ተቋማትና አጎራባች ከተማዎች ጋር መስራት፣አከባቢያቸውን የሚጠብቁ አዲስ ምልምል የሰላም ሰራዊት አባላትን በማሰልጠን አስመርቆ ወደስራ ማሰማራት ዋና ዋናዎቹ ናቸው ብለዋል።