የ6ወራት አግልግሎት አሰጣጥ ዕቅድ አፈፃፀም ዙሪያ ከተገልጋዮች እና ባለድርሻ አካላት ጋር ገመገመ።
ቢሮው በ2017 በጀት አመት የ6ወራት አግልግሎት አሰጣጥ ዕቅድ አፈፃፀም ዙሪያ ከተገልጋዮች እና ባለድርሻ አካላት ጋር ገመገመ።
ጥሪ 22/2017 ዓ.ም ( አዲስ አበባ )
******
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር በ2017 በጀት አመት የአገልግሎት አሠጣጥ የ6ወራት እቅድ አፈጻጸም በአራዳ ክ/ከተማ መሰብሰቢያ አደራሽ ከተለያዩ ተገልጋዮች እና ባለድርሻ አካላት ጋር ገምግመዋል።
በመድረኩ ላይ በመገኘት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የቢሮው ም/ቢሮ ሃላፊ አቶ ሚደክሳ ከበደ በቢሮው የሚሰጠውን አግልግሎት ግልፅ እና አሳተፊ ለማድረግ፣ የተገልጋይ እርካታ በማሳደግ አግልግሎት ሰጪ እና አግልግሎት ተቀባይ መካከል ጥብቅ ቁርኝት አመኔታ እና ፈጣን የአሰራር ስረዓትን በመዘርጋት አፈፃፀሙን ውጤታማ ለማድረግ መቻሉን ገልፀዋል።
ከዝምድና እና ከብልሹ አሰራሮች በፀዳ መልኩ አግልግሎት እንዲሰጥ ማድረግ መቻሉንና በዝህም ረገድ 1አመራር እና 5 ፈጻሚዎች ላይ ከቀላል እስከ ከባድ እርምት እርምጃ መወሰድ ተመቻሉን ተናግረዋል።
አቶ ሚደክሳ አክለውም የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት የማህበረሰብ ተኮር ወይይት ሥርዓት በመዘርጋት በርካታ ብሎኮች ላይ ተግባራዊ መደረጉን ጠቁመው በ6ወራት ውስጥም በተደረገ ዳሳዊ ጥናት 87% የውስጥ እና የውጪ የተገልጋይ 92%ማድረስ መቻሉን ገልጸዋል።
የስድስት ወራትየአገልግሎት አሰጣጥ ሪፖርት ያቀረቡት የቢሮው የአግልግሎት አሰጣጥ ክትትልና ድጋፍ ምዘና ዳይረክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ሃኒ አለሙ ሲሆኑ የግምገማው አላማ በምንሰጠው አግልግሎት ላይ ምን ብናደርግ የበለጠ ዕርካታ እንደምንጨምርና ። ወደፊት ምን ማስተካከል እንዳለብን ለማየት ነው ካሉ በኋላ በአግልግሎት አሰጣጥ እስታንዳርድ፣ በ2017 በጀት ዓመት የአግልግሎት አሰጣጡን መሻሻል፣ሌብነት እና ብልሹ አሰራርን ለመታገል የተሰሩ ስራዎች፣ በ6ወራት ውስጥ ያሉ ጠንካራ ጎኖች፣ ያጋጠሙ ችግሮችና የተወሰዱመፍትሔዎችን አብራርተዋል።
መድረኩን የመሩት ም/ቢሮ ሃላፊ አቶ ሚደክሳ ከበደ እና የቢሮው አማካሪ አቶ ገብረ ዳኘው የሆኑ ህዝቡን ማገልገል ክብር ነውና ሁሉም ሰራተኞች በትህትና እና በቅንነት ህብረተሰቡን ማገልገል ይገባል ካሉ በኋላ የአሸናፊነታችን ምስጥሩ የህብረተሰቡ ተሳተፎ ነውናየከተማችንን ሰላም ለማረጋገጥ የድርሻችን እንውጣ ብለዋል።
በመድረኩ ላይ የቢሮው ም/ቢሮ ሃላፊ አቶ ሚደክሳ ከበደ፣ የቢሮው አማካሪ አቶ ገብሬ ዳኘውን ጨምሮ የሃይማኖትአባቶች፣አባገዳዎችና ሀደ ሲንቄዎች እንዲሁም የተለያዩ ተገልጋዮች እና ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።