የ6 ወራት የመልካም አስተዳደር ዕቅድ አፈፃፀም...

image description
- recent news   

የ6 ወራት የመልካም አስተዳደር ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የ2017 በጀት ዓመት የ6 ወራት የመልካም አስተዳደር  ዕቅድ አፈፃፀም ገመገመ።

        ጥር  22/2017 ዓ.ም (አዲስ አበባ)

                        *******

ቢሮው የ2017 በጀት ዓመት የ6ወራት
የመልካም አስተዳደር ዕቅድ አፈፃፀም ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ግምገማዊ ውይይት አድርጓል።

በውይይቱ ወቅት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት ም/ል ቢሮ ኃላፊው አቶ ተስፋዬ ደንድር እንደተናገሩት  የውይይት መድረኩ ዋና ዓላማ በበጀት ዓመቱ ከሰላምና ፀጥታ አኳያ ህዝቡ ሊፈቱልኝ ይገባል ብሎ ከሰጠውን ኃላፊነት ምን ተሰራ? ምንስ ቀረ ? የሚለውን በጋራ መገምገም ነው ብለዋል።

የመወያያውን ሰነድ ያቀረቡ የቢሮው አማካሪ አቶ ገብሬ ዳኘው ሲሆኑ በገለጻቸውም፣በዝግጅት ምዕራፍ የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት፣ባለፉት 6 ወራት በዋናነት የአደባባይና የመንገድ ላይ ሃይማኖታዊ ስብከቶች፣ከጫኝና አውራጅ መመሪያ አተገባበር ጋር ተያይዞ ከህብረተሰቡ የተነሱ ቅሬታዎች፣ከትምህርት ቢሮ ጋር በትምህርት ጥራትና ሰላማዊ የመማርና ማስተማር ሂደቱን ከማስጠበቅአኳያ፣በከተማው የሚታዩ የኢኮኖሚ አሻጥርን መከላከል፣የቅጥር ጥበቃ አገልግሎት ከሚሰጡ አባላት ጋር ተያይዞ የሚነሱ ቅሬታዎችና ሌሎችም በርካታ የመልካም አስተዳደር ችግሮች መፈታታቸውን በሪፖርቱ አቅርበዋል።

ም/ል ቢሮ ኃላፊው አቶ ተስፋዬ ውይይቱን በመሩበት ወቅት እንደተናገሩት በከተማ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ፀረ-ሽብር ኃይሎችና ለሰላም ጠንቅ፣ለፀጥታ ስጋት የሚሆኑ ጉዳዮችና የመልካም አስተዳደር ችግሮች ላይ ትኩረት ሰጥተን መስራት አለብን ሲሉ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

በመጨረሻም በውይይቱ ተሳታፊዎች ለቀረቡ ጥያቄዎችና አስተያየቶች፣የመድረኩ አወያዮች ማብራሪያና ምላሽ ሰጥተውበታል።

 ም/ል ቢሮ ኃላፊው አቶ ተስፋዬ ደንድር፣የቢሮ አማካሪ አቶ ገብሬ ዳኘው ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተወጣጡ  ተሳታፊዎች በውይይቱ ላይ ተገኝተዋል።