ቴክኖሎጂዎችን ለማስተዋወቅና ሥራ ለማስጀመር የሚ...

image description
- recent news   

ቴክኖሎጂዎችን ለማስተዋወቅና ሥራ ለማስጀመር የሚረዳ ስልጠና ተሰጠ

የአገልግሎት አሰጣጥን ፈጣን፣ተደራሽና ቀልጣፋ ለማድረግ የሚረዱ  ቴክኖሎጂዎችን ለማስተዋወቅና ሥራ ለማስጀመር የሚረዳ ስልጠና ተሰጠ።

        ጥር  24/2017 ዓ.ም (አዲስ አበባ)

                        *****

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የአገልግሎት አሰጣጥን ፈጣን፣ተደራሽና ቀልጣፋ ለማድረግ  ያለማቸውን ቴክኖሎጂዎች ለማስተዋወቅና ሥራ ለማስጀመር የሚረዳ ስልጠና  ተሠጥቷል።

አቶ ገብሬ ዳኘው የቢሮው አማካሪ ስለለሙት ቴክኖሎጂዎች ባብራሩበት ወቅት  የበለፀጉ መተግበሪያዎች፣የኩነት ፍቃድ አገልግሎት፣
የሲትዝን ኢንጌጅመንትና ዌብሳይት መሆናቸውን ተናግረዋል።

በስልጠናው ወቅትም የፀጥታና የመረጃ ዘርፍ ም/ል ቢሮ ኃላፊ ኮምሽነር ቴዎድሮስ ወ/ሚካኤል በመክፈቻ ንግግራቸው እንዳሉት የዛሬው የቴክኖሎጂ ስልጠና ለከተማችን ሰላምና ደህንነ  ትልቅ እገዛ የሚያደርጉና ዜጎች ወደቢሮ ሳይመጡ ካሉበት ሆነው አገልግሎት የሚያገኙበት ብቻ ሳይሆን የተደራጀና ፈጣን የፀጥታ መረጃ ለማግኘት  የሚረዳ የቴክኖሎጂ  ነው ብለዋል።

በመተግበርያዎቹ አጠቃቀም ዙሪያ ስልጠና የሰጡት የፌደራል ፖሊስ  ባልደረባ የሆኑት ኢ/ር አለማየሁ ተሰማና የአዲስ አበባ ከተማ የኢንቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ የሶፍትዌር
ባለሙያ  ሂክማ ለማ ሲሆኑ በገለጻቸውም በቴክኖሎጂዎቹ ስለሚሰጠው አገልግሎትና  ከባለድርሻ አካላት የሚጠበቀው ተግባር፣
ዙሪያ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በመጨረሻም ከውይይቱ ተሳታፊዎች ለቀረቡ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ከአወያዮች ምላሽ ተሰጥቶበታል።

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ከማዕከል እስከ ወረዳ ያሉ አመራሮች፣
ዳይሬክተሬቶችና  ባለሙያዎች የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዳይሬክተሮችና የክ/ከተሞች አስተባባሪዎች የወረዳ ቡድን መሪዎች በስልጠናው ተገኝተዋል።