የእውቅና ሽልማት መረሃ ግብር

image description
- recent news   

የእውቅና ሽልማት መረሃ ግብር

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ከአዲስ አበባ ሴቶች ማህበር እውቅና እና ሽልማት ተበረከተለት ።

         ጥር 27/ 2017 ዓ/ም(አዲስ አበባ )

                         ****
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የከተማውን ሰላም አስተማማኝ ለማድረግ በሰራው ቅንጅታዊ ሥራና በተገኘው ውጤት ከአዲስ አበባ ሴቶች ማህበር  የዕውቅናና የሽልማት  ተበርክቶለታል።

በዕውቅናው መርሐ ግብር ላይ በመገኘት ዋንጫና የምሥክር ወረቀት ከተቀበሉ በኋላ ባስተላለፉት  መልዕክት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ም/ቢሮ ሀላፊ አቶ ሚደቅሳ ከበደ እንደተናገሩት ሴቶች የሰላም ባለቤት በመሆን፣ ሰላም እንዲረጋገጥና እንዲጸና በማድረጉ በኩል ላደረጉት አስተዋጽኦ ብቻ ሳይሆን በጋራ በመቀናጀት ለተገኘው ውጤት ስለተሠጠው ዕውቅና በቢሮውና በራሳቸው ስም ምስጋና አቀርበዋል።

በከተማው ውስጥ ካለው የህዝብ ብዛት የሴቶች ቁጥር ከፍተኛ እንደመሆኑ በርካታ ተግባራትን በጋራ እየተከናወኑ መሆኑንም ጠቅሰው ሰላም ሲረጋገጥና ሲጸና ቤተሰብ በሰላም ወጥቶ ይገባል፣የሰላም ዋጋ በምንም የሚተካ ስላልሆነ አሁን ያለውን አስተማማኝ ሰላም አጽንቶ ለማቆየት፣የወንጀል ምጣኔንና የደንብ ጥሰቶችንም ለመቀነስ በቀጣይ የተገኘውን ሰላም  አጠናክሮ ማስኬድ ይገባል ብለዋል።

በፕሮግራሙ ላይ ንግግር ያደረጉት ወ/ሮ እናት አለም እንዳለ የአዲስ አበባ ሴቶች ማህበር  ፕሬዝዳንት በበኩላቸው ስራዎቻችንን አጠናክረን እንድናስቀጥል ቢሮው በየግዜው የተለያዩ ስልጠናዎችን በመስጠትና ሴቶችን በማብቃት እንዲሁም በሰላምና በመልካም አስተዳደር ዙሪያ አብረን ለሰራናቸውና ስራዎችና ለመጣው ውጤት የተሰጠ ዕውቅና ነው ብለዋል ።

በመርሃ-ግብሩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ም/ቢሮ ሀላፊ አቶ ሚደቅሳ ከበደ፣የአዲስ አበባ ከተማ ሴቶች ማህበር  ፕሬዝዳንት ወ/ሮ እናት አለም እንዳለ ም/ፕሬዝዳንት ወ/ሮ አጸደ አበነ የማህበሩ እንዲሁም አመራሮችና የሁሉም ክ/ከተማ የሴቶች ማህበር ተወካዮች ተገኝተዋል ።