ፀጥታና ደህንነትን መከታተል የሚያስችል ሶፍት ዌር መተግበሪያ ላይ የተደረገው ውይይት ውይይት
የቢሮው ፀጥታና ደህንነትን መከታተል የሚያስችል ሶፍት ዌር መተግበሪያ ላይ ውይይት አደረገ ።
ጥር 28/ 2017 ዓ/ም(አዲስ አበባ )
**
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የጸጥታና ኦፕሬሽን ዘርፍ በከተማው ካሁን ቀደም በሰው ኃይል ብቻ የሚተገበሩ ሥራዎችን በቴክኖሎጂ በማስደገፍ ፈጣንና ተደራሽ ማድረግ የሚያስችሉ ናቸው ነው የተባለው።
ቢሮው የሚሠጣቸውን አገልግሎቶች በዘመናዊ ቴክናሎጂ በማስደገፍ የተቀላጠፈ ለማድረግ የሚያስችል ዘመኑን ያዋጀ ሶፍት ዌር ከአዲስ አበባ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ልማት ቢሮ ጋር በመተባበር አልምቶ ወደ ስራ ሊገባ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል።
ውይይቱን ያደረጉትየቢሮው የፀጥታ ኦፕሬሽንና ከኢኖቬሽን ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ከመጡ ባለሙያዎች ጋር ሲሆን ስራው የሚመለከታቸው የቢሮው የዘርፉ ሀላፊ፣ዳይሬክተርና ባለውያዎች የተሳተፉ ሲሆን ቴክኖሎጂው በአጭር ግዜ ውስጥ ተጠናቆ ሙሉ በሙሉ አገልግሎት እንደሚጀምር ለማወቅ ተችሏል።