የስድስት ወራት ዕቅድ ክለሳ

image description
- recent news   

የስድስት ወራት ዕቅድ ክለሳ

የቢሮው የሀይማኖትና ሰላም እሴት ግንባታ ዘርፍ የስድስት ወራት ዕቅድ ክለሳና ያለፈው የከተራና የጥምቀት በዓል አስመልክቶ ውይይት አደረጉ።

         ጥር 29/ 2017 ዓ/ም(አዲስ አበባ )

                         ****

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የሀይማኖት እና ሰላም እሴት ግንባታ ዘርፍ የስድስት ወራት ዕቅድ ክለሳና የከተራና የጥምቀት በዓልን አስመልክቶ ውይይት አካሂደዋል።

በውይይቱ መክፈቻ  ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ም/ቢሮ ሀላፊ አቶ ተስፋዬ ጫኜ እንዳሉት በፈጣሪ ፈቃድና በነበረው ርብርብ በዓሉ በሰላም እንዲጠናቀቅ ለማድረግ ተችሏል ያሉት ሀላፊው ሁሉም ማህበረሰብ፣ የጸጥታው አካል፣ ባለሙያውና፣ አመራሩ ሀላፊነትን በመውሰድ በዓሉ በሰላም እንዲጠናቀቅ በማድረግ በኩል ሰፊ ሚና እንደነበራቸው ተናግረዋል።

ከበዓሉ ቀደም ብሎ ህብረተሰቡንም በማወያየት የጸጥታ መደፍረስ እንዳይከሰት ተጽዕኖ መፍጠር እንደተቻለና ህብረተሰቡን የሰላም ባለቤት አድርጎ መስራትም ጠቀሜታው የጎላ መሆኑን አቶተስፋዬ ተናግረዋል።

የበዓሉ አከባበር ብሎም የዕቅድ ክለሳውን በተመለከተ  ሰነድ ያቀረቡት ወ/ሮ አዲስ አለም ዘነበ እና አቶ ኤልያስ ቀጄላ የስልጠና ባለሙያዎች ሲሆኑ በቀረበው ሰነድ ላይ ለተነሳው ሀሳብና አስተያየት ሀላፊው ምላሽ ሰተው ውይይቱ ተጠናቋል።

 በውይይቱ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ም/ቢሮ ሀላፊ አቶ ተስፋዬ ጫኜ፣የዘርፉ የክ/ከተማና ወረዳ አስተባባሪዎችና ቡድን መሪዎች ተሳትፈዋል።