የቀጠለ ዜና...

image description
- recent news   

የቀጠለ ዜና...

 

የአገልግሎት አሰጣጥን ቀልጣፋ ለማድረግ የሚረዱ  ቴክኖሎጂዎችን ለማስተዋወቅና ሥራ ለማስጀመር የሚያስችል  ስልጠና እንደቀጠለ ነው።

         የካቲት 01/2017 ዓ.ም (አዲስ አበባ)

                             ** **

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የአገልግሎት አሰጣጥንና የውስጥ አሰራርን ፈጣን፣ተደራሽና ቀልጣፋ ለማድረግ  ያለማቸውን ቴክኖሎጂዎች ለማስተዋወቅና ሥራ ለማስጀመር የሚረዳ ስልጠና  ተሠጥቷል።

የቢሮው አማካሪ አቶ ገብሬ ዳኘው የመክፈቻ ንግግር ባደረጉበት ወቅት የቢሮ ስራዎችን በቴክኖሎጂ ለማዘመን በ2016 በጀት ዓመት ሚያዝያ ወር ላይ እንደተጀመረ ጠቅሰው፣የዚህ ቴክኖሎጂ መዘረጋት ዋና ምክንያት የቢሮውን ተግባሮች ፈጣንና ቀልጣፉ እንዲሁም የከተማውን ሰላምና ደህንነት ለመጠበቅ ነው ብለዋል።

 አቶ ገብሬ አክለውም እንዳሉት የበለፀጉ መተግበሪያዎች፣የሁነት ፍቃድ አገልግሎት፣
የሲትዝን ኢንጌጅመንት፤ የቅሬታና አቤቱታ መጠቆሚያ፤ የመንግስት ጊዢ ኦንላይን መሆኑ፣የፀታና መረጃ ጥቆማ መስጫ ዌብሳይት መሆናቸውን ተናግረዋል።

በመተግበርያዎቹ አጠቃቀም ዙሪያ ስልጠና የሰጡት የፌደራል ፖሊስ  ባልደረባ የሆኑት ኢ/ር አለማየሁ ተሰማና የአዲስ አበባ ከተማ የኢንቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ የሶፍትዌር ባለሙያ  ሂክማ ለማ ሲሆኑ በገለጻቸውም በቴክኖሎጂዎቹ ስለሚሰጠው አገልግሎትና  ከባለድርሻ አካላት የሚጠበቀው ተግባር፣ዙሪያ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በስልጠናውም የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ከማዕከል እስከ ክፍለ ከተማ የሚገኙ የመረጃና ፀጥታ ዘርፍ ዳይሬክተር  አስተባባሪዎች፤ቡድን መሪዎችና  ባለሙያዎች ተገኝተዋል።

በመጨረሻም ከስልጠናው ተሳታፊዎች ለቀረቡ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ከአወያዮች ምላሽ ተሰጥቶበታል።