38ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ በተመለ...

image description
- recent news   

38ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ በተመለከተ በሰላም እንዲካሄድ ቅድመ ዝግጅት ውይይት

38ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ እና 46ኛው የስራ አስፈፃሚ ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ በሰላም እንዲጠናቀቅ የፀጥታና ደህንነት ቅድመ ዝግጅትን አስመልክቶ ውይይት ተደረገ ።

      የካቲት 3/ 2017 ዓ/ም(አዲስ አበባ )
                         **
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ  38ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ እና 46ኛው የስራ አስፈፃሚ ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ በሰላም እንዲጠናቀቅ የፀጥታና ደህንነት ቅድመ ዝግጅትንና ወቅታዊ የፀጥታ ሁኔታን አስመልክቶ ውይይት ተደርጓል።
      
በውይይቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ሀላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ እንደገለፁት በአዲስ አበባ  ከተማዋን የሚመጥን የጸጥታና የደህንነት ስራ ከምንግዜውም በበለጠ ሁኔታ እየተሰራ ነው ብለዋል።
 
የከተማችን ሰላም ዘላቂነት እንዲኖረው፣አልፎ አልፎ የሚስተዋሉ ወንጀሎችን ለመቀነስና ለመከላከል ህብረተሰቡ ፣ የጸጥታው አካላትና የሰላም ሰራዊትን ጨምሮ የተለያዩ አደረጃጀቶ
ችን ተሳትፎ በማጠናከር ከተማው ሰላማዊ እንዲሆን ማድረግ  እንደሚያስፈልግ ሀላፊዋ አሳስበዋል ።

በቅርቡ በከተማችን የሚካሄደው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ ድረስ ህብረተሰቡ በፍጹም ጨዋነት  የተለመደ እንግዳ ተቀባይነቱን በማሳየት ሀገር ከፍ ብላ እንድትደምቅ ሁሉም ሃላፊነቱን እንዲወጣ አደራ እላለሁ በማለት ተናግረዋል ።

በውይይቱ ላይ ወቅታዊ የፀጥታ ሁኔታና ለአፍሪካ ሕብረት ጉባኤ ሊኖር ስለሚገባው የፀጥታና የደህነት ቅድመ ዝግጅት ለውይይት መነሻ የሆነ ሰነድ ቀርቦ ውይይት ተካሂዶበታል።

የውይይት መድረኩን የመሩት አቶ ተስፋዬ ደንድር የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ም/ሀላፊ በበኩላቸው ከአሁን በፊት ሲሰራ ከነበረው በተለየ መልኩ የጸጥታ አመራሩ ሌሎችም በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች ህብረተሰቡን በማሳተፍና የሰላም ባለቤት በማድረግየከተማውን ዘላቂ ሰላምለማረጋገጥ
ወንጀሎችንና የጸጉረ ልውጥ እኩይ እንቅስቃሴዎችን በጋራ መከላከልና መቆጣጠር  እንደሚገባ አሳስበዋል ።

በውይይቱ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ሀላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ፣አቶ ተስፋዬ ደንድር የቢሮው ም/ሀላፊ ም/ኮማንደር ታዲዎስ አክሊሉ በአዲስ አበባ ፖሊስ የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት ዲቪዥን ኃላፊና ሌሎችም ጥሪ የተደረገላቸው የፀጥታ አካላት ተገኝተዋል ።