ከቢሮው ሰራተኞች ጋር ውይይት ተካሄደ
የመንግስት ቀጣይ ዋና ዋና የስራ አቅጣጫና ውሳኔዎችን በተመለከተ ከቢሮው ሰራተኞች ጋር ውይይት ተካሄደ ።
ታህሳስ 6/ 2017 ዓ/ም(አዲስ አበባ )
****
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የመንግስት ቀጣይ ዋና ዋና የስራ አቅጣጫና ውሳኔዎችን በተመለከተ ተወያይተዋል።
በውይይቱ ላይ ንግግር ያደረጉት አቶ ሚደቅሳ ከበደ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ም/ቢሮ ሀላፊ እንደተናገሩት በመንግሥት የሚመራ የህዝብን ዕውቀና ያገኘ ገዥ ፓርቲ እንዳለ በመጠቆም ከምርጫ በኋላ እፈጽማለሁ ብሎ ቃል የገባቸውን እየፈጸመ የሚገኝ ፓርቲ ነው ብለዋል።
እንደ ሀገር ለመጣው ድልና ውጤት የመላው መንግሥት ሰራተኛ አሻራ ስላለበት የመጣውን ውጤት አጠንክሮ አስተማማኝና ዘላቂ ሰላም አጽንቶ ለማቆየት ለሀገሬ ምን ሰራሁ ብሎ እራስን መጠየቅ ይገባልም ሲሉ ገልጸዋል።
በዚሁ ውይይት ላይ አቶ ገብሬ ዳኘው የቢሮው አማካሪ እንደተናገሩት በለውጡ መንግሥት አዋጆች፣ደንቦችና መመሪያዎችን ከህዝብ ጋር የጋራ በማድረግና የመተግበር ስራ እየተከናወነ በመሆኑ ውጤታማ ስራ መሰራቱን ጠቅሰው የህግ የበላይነትንና ፍትሀዊነትን ከማረጋገጥ አኳያ አገልግሎት ሰጪ ተቋም እንደመሆናችን መጠን ሁሉም ሀላፊነት ወስዶ ሊሰራ ይገባል ብለዋል።
ለውይይቱ መነሻ የሚሆን ሰነድ ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል።
በውይይቱ ላይ የቢሮው ምሀላፊ፣አማካሪዎች፣
አጠቃላይ የተቋሙ ሰራተኞች ተሳትፈዋል ።