ለሰላም ሰራዊትና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች...

image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

ለሰላም ሰራዊትና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የስራ ስምሪት ተሰጠ ።

ቢሮው 38ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ በሰላም ተጀምሮ እንዲጠናቀቅ ለማድረግ ለሰላም ሰራዊትና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የስራ ስምሪት ሰጥቷል።

የካቲት 6/2017 ዓ.ም ( አዲስ አበባ )

********

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የህዝብ የአደረጃጀት ዘርፍ 38ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ በሰላም ተጀምሮ እንዲጠናቀቅ ለማድረግ ለሰላም ሰራዊትና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የስራ ስምሪት ሰጠ ።

መድረኩ ላይ በመገኘት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የቢሮው ም/ቢሮ ሃላፊ አቶ ሚደክሳ ከበደ የሰላም ሰራዊት የተለያዩ የአደባባይ በዓላት በሰላም ተከብሮ ማለፉ በቀንና በለሊት ደከመኝ ሰለቸኝ ሳትሉ በመስራታቸችሁ ነውና ትልቁን ሚና ስለወጣቹ ምስጋና ይገባችኋል ካሉ ቦበኋላ የዛሬው መድረክ 38ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ በሰላም ተጀምሮ እንዲጠናቀቅ ለማድረግ ከወረዳ እስከ ብሎክ ድረስ ውይይትና ስምሪት ሲሰጥ ቆይቶ ዛሬ እንደ ከተማ ማጠቃለያ መሆኑን ተጠቁመው ጉባኤው የአገራችንን ገፅታ ለዓለም ሕብረተሰብ የሚያሳይ፣ ኢኮኖሚያዊና ዲፕሎማሲያዊ ፋይዳ ያለው ነውና ምንም የጸጥታ ችግር ሳይከሰት እንዲከናወን ማድረግ፣ወደ አገራችን የሚመጡ እንግዶችን በእትዮጵያዊ ጨዋነት በመቀበልና ቅድሚያ በመስጠት ማስተናገድ ይኖርብናል ብለዋል ።

በመድረኩ ላይ የአራዳ ክፍለ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ አብዲ ሙሉነህ እንደተናገሩት እንግዶቹ አገራችን እንዲናፍቁና ሌላ ግዜም ለመዝናናት መርጠው እንዲመጡ ምቹ የሆነች ከተማ ለማድረግ እንስራ ፣ በቂ ጥበቃና ፣ ፈጣን የመረጃ ልውውጥ ተግባራዊ ማድረግ፣ እንግዳ ተኮር ሌብነት እንዳይከሰት የወንጀል መከላከል ስራ መስራት ይጠበቅብናል ብለዋል።

የመወያያ ሰነድ ያቀረቡት የዘርፉ ባለሙያ አቶ አብረሃም እንግዳወርቅ ሲሆኑ የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ ታሪክ፣ ማህበራዊ ፉይዳው፣ ለአገራችን ያለው ጥቅሜታ፣ ዘንድሮ የሚካሄደው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ ቅድመ ዝግጅት፣ጉባኤው በሰላም እንዲጠናቀቅ ከሰላም ሰራዊት የሚጠበቅ ሚናን በዝርዝር አብራርተዋል።

በመድረኩ ላይም የቢሮው ም/ቢሮ ሃላፊ አቶ ሚደክሳ ከበደን ጨምሮ ከ11ዱ ክ/ከተሞች የተወጣጡ የሰላም ሰራዊትና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍል ተወካዮች ተገኝተዋል።