የእውቅናና የምስጋና መረሃ-ግብር

image description
- recent news   

የእውቅናና የምስጋና መረሃ-ግብር

"ከተማችን አዲስ አበባ  ከአገራችን ርዕሰ ከተማነት ባሻገር የአፍሪካ መዲና እና በርካታ አለም አቀፍ ዲፕሎማቶች  መቀመጫ በመሆኗ ደረጃዋን የሚመጥን ዘመናዊ የፀጥታና ህግ አስከባሪ ተቋማት ሊኖራት ይገባል"

ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ  የአዲስ አበባ ከተማ  ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ሃላፊ

     የካቲት 15/2017 ዓ.ም ( አዲስ አበባ )

                   ******

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ ቢሮ በ2017 በጀት ዓመት የተካሄዱት ህዝባዊ፣ ሃይማኖታዊና ባህላዊ የአደባባይ በዓላት፣አገር አቀፍና አህጉር አቀፍ ጉባዔዎችና ኮንፈራንሶች በስኬት እንዲጠናቀቅ  ላደረጉ ለሰላም ሰራዊት አባላት እና ለፀጥታ አካላት የእውቅናና የምስጋና መረሃ-ግብር  ተካሂዷል።

በመድረኩ ላይ በመገኘት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ሃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ  በ2017 በጀት ዓመት የተካሄዱት ህዝባዊ፣ ሃይማኖታዊና ባህላዊ የአደባባይ በዓላትና በከተማችን የተከናወኑ አለማቀፋዊ፣አህጉር አቀፋዊ፣ አገራዊ እንዲሁም ከተማዊ ትላልቅ ሁነቶች በስኬት ስለተጠናቀቁ  ሁሉም የፀጥታ ሃይሎች እና የሰላም ሰራዊት አባላት ትልቁ ሚና ስለተወጣችሁ በቢሮው ስም አመስግናለሁ ብለዋል።

ከተማችን አዲስ አበባ  ከአገራችን ርዕሰ ከተማነት ባሻገር የአፍሪካ መዲና እና በርካታ አለም አቀፍ ዲፕሎማቶች  መቀመጫ በመሆኗ ደረጃዋን የሚመጥን ዘመናዊ የፀጥታና ህግ አስከባሪ ተቋማት ሊኖራት ይገባል ብለዋል። 

ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ አክለውም ከተማችን በኮሪደር ልማት እንደ ስሟ አበባ ሆናለችና በኮሪደር የተዘጋጀ የተቀናጀ ልማት ስራ ምከንያት የፀጥታና ደህንነት ስራችን በእጅጉ የሚያግዙ መሰረተ ልማቶች መሰራታቸውን ጠቅሰው  ቢሮአችን የከተማዋን ሰላም ለማረጋገጥ በትጋት እየሰራ ሲሆን ከ252 ሺ በላይ የሰላም ሰራዊት አባላትን  የንድፈ ሃሳብና የተግባር ስልጠና በመስጠት ህብረተሰቡን የሰላም ባለቤት ማድረግ ተልዕኳችንንበማሳካት ላይ እንገኛለን ብለዋል። አሁንም ከፊታችን የሚከበረው 129ኛ የአድዋ ድል በአልም በሰላም እንዲከበር ለማድረግ ሁላችንም ድርሻችንን እንድንወጣ አደራ እላለሁ ብለዋል።

የቢሮው ም/ቢሮ ሃላፊ አቶ ሚደክሳ ከበደ በበኩላቸው ባደረጉት ንግግር የሰላም ሰራዊት አደረጃጀት በተባበረና በተቀናጀ የፀጥታ አስተዳደር ስርአት የአዲስ አበባን ሰላም የሚያፀና መሆኑን ጠቅሰው ቢሯችን የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ የህግ የበላይነትን በማረጋገጥ በመዲናዋ ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን ከተለያዩ ባለ ድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት ይሠራል ብለዋል።

በመርሃ-ግብሩ ላይ ለአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎት ዲቪዚዮን፣
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር  ባለሥልጣን፣
ለአዲስ አበባ ከተማ ህብረተሰብ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ኮሚሽን፣ለክፍለ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ፅ/ቤቶችና ለሠላም ሠራዊት ተወካዮች ኪሪስታል ዋንጫ፣ዋንጫና የምስክር ወረቀት ተሰጥቷቸዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ  ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ሃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊድያ ግርማ፣ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ሥራ አሥኪያጅ፣የቢሮው ም/ቢሮ ሃላፊዎች፣የቢሮው አማካሪዎች የክፍለ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ፅ/ቤት ኃላፊዎችን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።