የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና
በጎ ፈቃደኝነት ከውስጥ በመነጨ ውስጣዊ መልካምነት የሚሠጥ አገልግሎት ነው።
አቶ ተስፋዬ ጫኔ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ም/ቢሮ ሀላፊ
ታህሳስ 21/ 2017 ዓ/ም(አዲስ አበባ )
** **
ለብሔራዊ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች በሰላም እሴት ግንባታ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ።
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የሀይማኖት እና ሰላም እሴት ግንባታ ዘርፍ ከሁሉም ክ/ከተማ ለተወጣጡ ብሔራዊ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች በሰላም እሴት ግንባታ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል።
በመድረኩ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት አቶ ተስፋዬ ጫኔ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ም/ቢሮ ሀላፊ በከተማው ላይ በርካታ ስራዎችን ሳትሰለቹ በብዙ ውጣ ውረድ ውስጥ በመሆን እየሰራችሁ ላላችሁት ስራ ምስጋና ይገባችኋል ያሉት ሀላፊው በጎ ፈቃደኝነት ከውስጥ በመነጨ መልካምነት የሚሰጥ አገልግሎት ሲሆን ይህም ስልጠና የበለጠ አቅም የሚገነባ ነው ሲሉ ተደምጠዋል
እንደ ሀገር በበጎ ፈቃድ አገልግሎት መሳተፉ የህሊና እርካታ ከመስጠቱም በላይ የውስጥ መሰጠትን የሚጠይቅ ተግባር እንደ መሆኑ መጠን በዚህ ውስጥ ማለፍ እድለኝነትም ነው ብለዋል።
የስልጠናውን ሰነዱን ያቀረቡት ወ/ሮ አዲስ አለም ዘነበ የሀይማኖት እና ሰላም እሴት ዘርፍ የስልጠና ባለሙያ ሲሆኑ በዘላቂ ሰላም እሴት ግንባታ ሂደት የበጎ ፈቃድ ወጣቶች ትብብርና ተሳትፎ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባና በሁሉም አካባቢዎች የሚገኙ ጠቃሚ እሴቶችን በማሳደግ ለሰላም ግንባታ የሚሰጠው የበጎ ፈቃደኝነት አገልግሎት ጥቅሙ ለማህበረሰቡ እና ለራስ እርካታ መሆኑን በሰነዱ ጠቁመዋል ።