የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና
በሰላም፤ በጸጥታና በልማት ዙሪያ ተሳትፎን ለማጎልበት ለሲቪክ እና ብዙሃን ማህበራት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ።
ታህሳስ 27/ 2017 ዓ/ም (አዲስ አበባ )
**
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ በሰላም በጸጥታና በልማት ዙሪያ ተሳትፎን ለማጎልበት ለሲቪክ እና ለብዙሃን ማህበራት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል።
የመወያያ ሰነዱን ያቀረቡት አቶ ውድነህ አቢ የቢሮው የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ ቡድን መሪ ሲሆኑ በሰነዱም በአዲስ አበባ ከተማ ዉስጥ 150 የሲቪክና የብዙሃን ማህበራት እንደሚገኙ በመጥቀስ ቢሮው በአዋጅ ከተሰጠው ስልጣንና ተግባር አንዱ ህዝቡን በማደራጀት በሰላም ዙሪያ ከተለያዩ የህብረተሰቡ ክፍሎች ጋር በመስራት የከተማውን ነዋሪ የሰላም ባለቤት ማድረግ ሲሆን የተደራጁ የሲቪክ እና የብዙሃን ማህበራት ህግን አክብረው እንዲሰሩ ማድረግ፣ ህብረ ብሔራዊ ወንድማማችነትንና እርስ በርስ መከባበር፤መቻቻል እንዲሁም ትብብር በማድረግ አብሮነትን ማረጋግጥ፤የዜጎችን ተሳትፎ ማጎልበት፤የጥላቻ ትርክቶችን ወደ ጎን በመተው በልማቱ፤በሰላምና ጸጥታ ጉዳዮች ላይ በጋራ መሥራ እንደሚገባ ተብራርቷል ።
በስልጠናው ላይ የሲቪክና የብዙሃን ማህበራት ተወካዮችና እንዲሁም የቢሮው የማዕከልና የክፍለከተማ ቡድን መሪዎችና አስተባባሪዎች ተሳትፈዋል፡፡