በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት አካሄደ።
የቢሮው የሀይማኖት እና ሰላም እሴት ግንባታ ዘርፍ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት አካሄደ።
መጋቢት2/2017 ዓ.ም (አዲስ አበባ)
*********
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የሀይማኖት እና ሰላም እሴት ግንባታ ዘርፍ ወቅታዊ ጉዳዮችን በተመለከተ ከሁሉም ክ/ከተማዎች ከተወጣጡ የዘርፉ አስተባባሪዎችና ቡድን መሪዎች ጋር ተወያይተዋል ።
አቶ ተስፋዬ ጫኔ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የሀይማኖት እና ሰላም እሴት ግንባታ ዘርፍ ም/ቢሮ ሀላፊ በውይይቱ ላይ እንደተናገሩት በአዲስ አበባ ከተማ የሁሉም ኃይማኖቶች አስተምህሮ እና የመቻቻል እሴት ለከተማችን ዘላቂ ሰላም መሰረቶች ሆነው የቆዩ እንደሆኑ ጠቅሰዋል፡፡
ነገር ግን አልፎ አልፎ በአንዳንድ ግለሰቦች ንግግርና የቃላት መወራወር አንዱ የሌላውን ሃይማኖት የማንኳሰስ ድርጊቶች በማህበራዊ ሚዲያዎች ሳይቀር እየተለለፉ እንደሚገኙ ጠቅሰው እነዚህ አላስፈላጊ ድርጊቶች እየቆዩ ሲሄዱ ግን እንደ ሀገር በርካታ ችግሮች እንደሚያመጡ በመረዳት የሚስተዋሉ አዝማሚያዎችን ቀድሞ በመለየት የፀጥታ ስጋት ሆኖ የሰላም እጦትን ይዞ እንዳይመጣ መጠንቀቅ ይገባልም ሲሉ ተደምጠዋል ።
ሀላፊው አያይዘውም መረጃዎችን በፍጥነት በመቀባበል ያሉትን ክፍተቶች በመለየት በከተማው ውስጥ እየተናፈሰ ያለው የሀይማኖት ጉዳይ በትኩረት ልንከታተለው ይገባል ካሉ በኃላ የታየው አዝማሚያ ምን ችግር ይዞ እንደሚመጣ መገመት አስቸጋሪ ስለማይሆን ያገኘነውን ሰላም በዘላቂነት ለማስቀጠል በጋራ መስራት ይጠበቅብናል ብለዋል ።