የቴክኖሎጂ ውጤቶች

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

የቴክኖሎጂ ውጤቶች

ቢሮው የሚሰጣቸውን አግልግሎቶች ፈጣን፣ ቀልጣፋና ለህብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግ ያለማቸውን የቴክኖሎጂ ውጤቶችን አስተዋውቆ መደበኛ አገልግሎት አስጀመረ።

መጋቢት 04/2017ዓ.ም ( አዲስ አበባ )

* * *

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የሚሰጣቸውን አግልግሎቶች ፈጣን፣ ቀልጣፋና ለህብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግ ያለማቸውን የቴክኖሎጂ ውጤቶች መደበኛ አገልግሎት አስተዋውቆ አስጀምሯዋል።

በመርሃግብሩ ላይ የቢሮው ሃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊድያ ግርማን ጨምሮ የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ሥራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ፣የቢሮው ም/ቢሮ ሃላፊዎች፣ የቢሮ አማካሪዎች፣ የፀጥታና መረጃ ዘርፍ ዳይረክተር እና ባለሙያዎች፣ የክ/ከተማ የጽ/ቤቱቶች ሃላፊዎችና አስተባባሪዎች፣ የፈደራል ፖሊስ አመራሮችና አባላት፣ ከሁሉም ክ/ከተማ የተወጣጡ የሰላም ሰራዊት አባላት ተገኝተዋል።

መድረኩ ላይ በመገኘት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ ከተማችን አዲስ አበባ እንደ ስሟ ውብና ስማርት በመሆኗ ከምን ግዜም በላይ ጠንካራ ፀጥታና ደህንነት የሚጠብቅ አደረጃጀት ያስፈልጋል።

ስለዚህ ቢሯችንም ከህብረተሰቡ የተወጣጣ ተልዕኮውን የሚወጣ ጠንካራ አደረጃጀት በመፍጠርና ከተለያዩ የፀጥታ መዋቅር ጋርም በመቀናጀት በትጋት እየሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡

የቢሮ ኃላፊዋ አክለውም አሁንም ቢሮው ከወረቀት ነፃ የሆነ፣ ስራችን ቀልጣፋና ተደራሽ ለማድረግ ያለመ ማዕከል በማቀቋቋም ጊዜውን የዋጁ አስር የሚሆኑ የቴክኖሎጅ ሲስተሞችን በ2017 በጀት ዓመት በማልማት የሙከራ ትግባራ ላይ እንደነበር ጠቅሰው በዘሬው ዕለት በይፋ መደበኛ አገልግሎቱን አስጀምረዋል።

በዚህም ቢሮው 8882 የነፃ የስልክ ጥሪ ማዕከል፣ የድረ ገጽ፣ የዜጎች ተሳትፎ መተግበሪያ፣ አሴት ማኔጅመንት፣ ቪዲዮ ኮንፍረንስን ጨምሮ ሌሎች የቴክኖሎጂ ስራዎችን ይፋ አድርጓል።

በመጨረሻም ክብርት የቢሮ ኃላፊዋ፤ የሚዲያ አካላትና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የጥሪ ማዕከሉን ጎብኝተዋል፡፡