የሶስተኛ ሩብ ዓመት የመልካም አስተዳደር እቅድ...

image description
image description
image description
image description
- recent news   

የሶስተኛ ሩብ ዓመት የመልካም አስተዳደር እቅድ አፈፀፀም

ቢሮ የ2017 በጀት አመት የሶስተኛ ሩብ ዓመት የመልካም አስተዳደር እቅድ አፈፀፀም ላይ ከማዕከል እስከ ክፍለ ከተማ ከሚገኙ የመልካም አስተዳደር ተወካዮች ጋር ገመገመ ።

መጋቢት 04/2017ዓ.ም ( አዲስ አበባ )

****

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የ2017 በጀት አመት የሶስተኛ ሩብ ዓመት የመልካም አስተዳደር እቅድ አፈፀፀም ላይ ከማዕከል እስከ ክፍለ ከተማ ከሚገኙ የመልካም አስተዳደር ተወካዮች ጋር ገምግሟል፡፡

በግምገማው ወቅት የቢሮው አማከሪ አቶ ገብሬ ዳኘው እንደተናገሩት አስቀድማው ከተለዩ ከአስራ አንድ የመልካም አስተዳደር ችግሮች መካከል ዘጠኙ የተፈቱ ቢሆንም አሁንም ያልተፈቱና በሂደት ላይ ያሉ አራት የመልካም አስተዳደር ችግሮች መኖራቸውንና በቅርቡ የሚፈቱ መሆኑ ገልጸዋል።

ስራው በውክልና እየተሰራ ያለ ቢሆንም የመልካም አስተዳደር ስራ ከፍተኛ ስለሆነ በትጋት መሰራት ይገባል ካሉ በኃላ አፈፃፀሙን እስከታች ወርደን ስለምናይ መረጃው በአግባቡ ተደራጅቶ ሊቀመጥ ይገባል ብለዋል።

አንዳንድ ወረዳዎች የወንጀለኞች መደበቅያ የሆኑ ሥፍራዎች፣አግልግሎት የማይሰጡ ባሶች፣የፖሊስ ኮሚኒቲ አገልግሎትአለመስጠት፣

የፖሊስ ማዕከል አገልግሎት ጥሪ አለመኖሩ እንዲሁም በሃይማኖት ተቋማት የውስጥ ችግሮች እና የድምፅ ብክለት የመልካም አስተዳደር ችግሮች እንደነበሩ ጠቅሰው በርከታ ችግሮች ከተሰብሳቢዎቹ ሃሳብ ለመረዳት ተችሏል፡፡