የቅንጅታዊ ሥራ ተገመገመ
በከተማው ላይ ቅንጅታዊ ስራዎች በመሰራታቸው የወንጀል ምጣኔን መቀነስ መቻሉ ተገለፀ ።
መጋቢት 04/2017ዓ.ም ( አዲስ አበባ )
* * *
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ በከተማው ላይ በየግዜው የሚከሰቱ ወንጀሎችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር አበክሮ እየሰረ መሆኑን በዛሬው ዕለት የቅንጅታዊ ሥራ በተገመገመበት ወቅት ተገልጿል።
ቢሮው ካሁን በፊት በቅንጅት አብሮ ከሚሠራ ቸው ተቋማት ጋር የጋራ የማስፈጸሚያ ዕቅድ አውጥቶ ወደ ስራ መግባቱ የሚታወቅ ሲሆን በታቀደው መሰረት የተሰሩ ስራዎች አፈፃፀምና ያጋጠሙ ችግሮችን ገምግሟል።
የግምገማ ውይይቱን የመሩት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ሀላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ እንዳሉት በቅንጅታዊ አሠራሩ በታቀደው ልክ በመሰራቱ የወንጀል ምጣኔን ለመቀነስ አግዞናል፣ የመንገድ ዳር መብራቶች መዘርጋታቸውና ህብረተሰቡ በየአካባቢው መብራቶችን እንዲጠቀም መደረጉ በተወሰነ መንገድ ወንጀሎች እንዲቀንሱ ቢያደርጉም አሁንም አልፎ አልፎ ክስተቱ እንዳለ ጠቁመው ቢሮው የተለያዩ አደረጃጀቶችን በመፍጠር እና ህብረተሰቡንም የሰላም ባለቤት ማድረጉን ቀጣይ በማድረግ የወንጀል ምጣኔን ከዚህ የበለጠ ለመቀነስ መሥራት ይጠበቅብናል ሲሉ ተደምጠዋል ።
አሁን ላይ ያጋጠሙ ችግሮችን በቀጣይ በማስተካከልና ለወንጀል መበራከት መንስኤ የሆኑ ምክንያቶችንም ለይቶ መቅረፍ እንደሚገባ ክብርት የቢሮ ሀላፊዋ ተናግረዋል ።