የተርሚናል አገልግሎት አሰራር

image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

የተርሚናል አገልግሎት አሰራር

የአዲስ አበባ ከተማ የተርሚናል አገልግሎት አሰራርና ቁጥጥር ደንብና የማስፈጸሚያ እቅድ ላይ ውይይት ተደረገ።

መጋቢት 05/2017ዓ.ም

(አዲስ አበባ )

* * * * *

በቅርቡ በከተማው ካቢኔ የጸደቀዉ የተርሚናል አገልግሎት አሰራርና ቁጥጥር ደንብ ላይ ግንዛቤ ለመፍጠር በየደረጃው ከሚገኙ አመራሮች ጋር ውይይት ተደርጎል።

መድረኩን የመሩት የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ሀላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ እና አቶ ያብባል አዲስ የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ ሀላፊ ሲሆኑ በከተማችን ከሚነሱ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ውስጥ አንዱና ዋናው የትራንስፓርት አገልግሎት ቅልጥፍና ፍትሀዊነትና እንዲሁም ብቁ ስምሪት የመስጠት ጉድለት አንዱ ነው። ስለሆነ በተርሚናል የተደራጁ ወጣቶች የተደራጁበት አላማ ለወጣቶች ስራ መፍጠር ቢሆንም የአሰራር ስርአት ባለመኖሩ ምክንያት ለተለያዩ ብልሽቶች ተጋልጧል።

አንዳንድ የተደራጁ ማህበራት በተለያዩ ማህበራዊ አገልግሎቶችና ሰላምና ጸጥታ በማስከበር ረገድ በጎ አስተዋጾ ያደረጉ ሲሆን ሌሎች የተደራጁ ማህበራት ለረጅም አመታት ተርሚናሎቹ ከመቆጣጠራቸው በላይ ከታሪፍ በላይ በማስከፈል እና ፀያፍ ቃላቶችን በመናገር ህዝብን የሚያማርሩ ግለሰቦች ስለነበር የከተማችንን ሰላም ዘላቂ ለማድረግ ደንቡ እንዳስፈለገ እና ተግባራዊ እንደሚሆን ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ ገልጿል።

አቶ ያብባልም በበኩላቸው በከተማችን የትራንስፖርት አቅርቦት፣ የትራፊክ መጨናነቅና የትራንስፖርት አገልግሎት የአደረጃጀት ችግሮች ነበር። ከነዚህ ችግሮች መካከል የተራአስከባሪዎችን በመቅጠር ችግሮችን በማባባስ ህዝቡን ወደምሬት ስለሚያስገባ ደንቡ እነኚህ ችግሮች የሚቀርፍ መሆኑንና የትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጥን ደህንነት ለመሻሻል ነው ብለዋል።

ደንቡ ላይ ማብራሪያ የሰጡት የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ ም/ቢሮ ሀላፊ አቶ ደኛቸው ሽፈራው ደንቡን ለማዘጋጀት መነሻና ምክንያቱ፣የደንቡ አስፈላጊነት፣ጠቅላላ ድንጋጌዎች፣የባለድርሻ አካላት ሚና እና የባለድርሻ አካላት ሚና፣ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮች እና መፍትሔው በዝርዝር አብራርተዋል።

የአገልግሎት አሰጣጥን ቀልጣፋ፣ተደራሽና ፍትሃዊ ለማድረግ፣የካሁን ቀደሙን የታክሲ ተራ አስከባሪዎች አግልግሎት አሠጣጥን ለማሻሻል ቢሮው የተርሚናል አግልግሎት አሰራርና ቁጥጥር ደንብ አዘጋጅቶ በከተማ ካቢኔው ማፀደቁን ም/ቢሮ ኃላፊው ገልፀዋል።

ደንቡ የበርካታ ጊዜ የህብረተሰብ ጥያቄን የሚፈታ፣ ፍትሃዊነትንም የሚያሰፍን፣

አገልግሎትን የሚያሳልጥ፣ሰላምና ደህንነትን የሚያሳፍን መሆኑን የስብሰባው ተሳታፊ አመራሮች ተናግረዋል።

ውይይቱን የመሩት ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማየአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ እና አቶ ያብባል አዲስ የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ ሀላፊ የተለያዩ የአፈፃፀም አቅጣጫዎችን አስቀምጠዋል።

በመድረኩ ላይም ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊን ጨምሮ ፣አቶ ተስፋዬ ደንድር የቢሮው ም/ሃላፊ፣ አቶ ያብባል አዲስ የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ ሀላፊ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ ም/ቢሮ ሀላፊ አቶ ዳኛቸው ሽፈራ፣ የአዲስ አበባ ስራና ክህሎት ቢሮ ም/ቢሮ ሀላፊ አቶ መሀመድ እና የሁሉም ክፍለ ከተማና ወረዳ የሰላምና ጸጥታ ጽ/ቤት ሀላፊዎች፣የትራንስፖርት ቢሮና የስራና ክህሎት ጽ/ቤት አመራሮች ተገኝተዋል።