ዓለማቀፍ የሴቶች ቀን

image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

ዓለማቀፍ የሴቶች ቀን

ዓለማቀፍ የሴቶች ቀን ተከበረ

መጋቢት 8/2017 ዓ.ም(አዲስ አበባ)

*****

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የማዕከል ሰራተኞች ዘንድሮ በአለም አቀፍ ደረጃ ለ114ኛ ጊዜ በአገራችን ደግሞ ለ49ኛ ጊዜ "ፈጣን ቀጣይነት ያለው ሁሉን አቀፍ ለውጥ በሴቶች ተሳትፎ ይረጋገጣል" በሚል መሪ ቃል አለም የሴቶች ቀንን አከብረዋል።

በፕሮግራሙ ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉት የቢሮው አማካሪ አቶ ገብሬ ዳኘው አሁን ካለው የሀገራችን ነባራዊ ሁኔታ በመነሳት መሪ ቃሉ እራሱ እንደሚነግረን በአለማችን ብሎም በሀገራችን ጥቁር ነጭ ሳይባል ፍትሀዊ የሆነ አሰራርን ለማስፈን በማሰብ ነው በዓሉ በየዓመቱ የሚከበረው ብለዋል፡፡

በአገራችን ዉስጥ ሲንከባለሉ የመጡ በርካታ ችግሮች ቢኖሩም የሴቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎ ለማረጋገጥ ዘርፈ ብዙ ሥራዎች በመሰራታቸው

በአገራችን ዉሰጥ በመጣው የዕድገት ለውጥ ውስጥ የሴቶች ተሳትፎ የጎላ እንደነበረ ተናግረዋል፡፡

በዓሉን በማስመልከት የቢሮው የሴቶች ተጠሪ ወ/ሮ አዲስ አለም ዘነበ ሰነድ ያቀረቡ ሲሆን ወ/ሮ አበበች አድማሱ ደግሞ ግጥም አቅርበዋል፡፡