



የልምድ ልውውጥ
የአዲሰ አበባ ከተማ አስተዳደር የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ከአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ጋር የልምድ ልውውጥ አደረገ።
መጋቢት10/2017 ዓ.ም
*****
የሰው ሀብት አስተዳደር ቢሮ ከአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ጋር የልምድ ልውውጥ አድርጓል።
ለልምድ ልውውጡ ለመጣው ቡድን ስለ አዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ አደረጃጀትና አጠቃላይ የስራ ሂደት ማብራሪያ የሰጡት የቢሮው ም/ቢሮ ሀላፊ አቶ ሚደክሳ ከበደ እንደተናገሩት ቢሮው በቅርብ ግዜ የተቋቋመ ቢሆንም ዘርፈ ብዙ ስራዎች እየሰራ መሆኑን ጠቅሰው አራት ዘርፎች ማለትም የፀጥታና መረጃ፣የህዝብ አደረጃጀት፣ ሰላም እሴት ግንባታና የፀጥታ ኦፕሬሽን ዘርፍ ያለውና 4ቱም በም/ል ቢሮ ሀላፊዎች የሚመራ እንዲሁም በርካታ ዳይሬክቶሬቶች ቡድን መሪዎችና ሰራተኞች አቅፎ በአዋጅ የተቋቋመ የከተማዋ ቁልፍ ቢሮ መሆኑን አንስተዋል።
መዋቅሩም በክ/ከተማና ወረዳ ደረጃ ተዋቅሮ የከተማዋ ሰላምና ደህንነት ለመጠበቅ ሌት ተቀን እየተጋ ያለ ቢሮ መሆኑን ገልጸው፣የአዲስ አበባ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ከተማችን የደረሰችበትን የእድገትና የለውጥ ደረጃ መሰረት ያደረገ ሪፎርም ተሰርቶ መጠናቀቁንም አንስተዋል።
ቢሮው ከሌሎች የፀጥታ ሀይሎች ጋር በመቀናጀት የፀጥታ ስጋት የሆኑ ህገ-ወጥ ተግባራትን ማለትም የኑሮ ውድነት የሚያባብሱ፣ትራንስፖርት እጥረት እንዲፈጠር የሚያደርጉ፣ የመልካም አስተዳደር ችግር የሚፈጥሩ፤ ለብልሹ አሰራር የተጋለጡና እና ሌሎች የጸጥታ ስጋት የሆኑ ጉዳዮች ላይ በመወያየት ህብረተሰቡ ከፀጥታ ኃይል ጎን እንዲቆም ከማድረጉም በላይ ከሁሉም የጸጥታ ሀይሎች የተውጣጣ ግብረ-ሀይል ተቋቁሞ፤ የማስፈፀሚያ ዕቅድ በማዘጋጀትና በመገምገም እንደሚሰራም ገልጸፀውላቸዋል።
አቶ ገብሬ ዳኘው የቢሮው አማካሪ በበኩላቸው አገልግሎት አሰጣጣችንን ፈጣንና ቀልጣፋ ለማድረግ ማህበረሰቡ ካለምንም እንግልት ቤቱ ሆኖ ጥቆማ እንዲሰጥና አገልግሎትም እንዲያገኝ የመረጃ መረብ ለምቶ ወደ ተግባር መግባቱን ገልጸዋል።
የልምድ ልውውጥ ያደርጉ ቡድኖቹም ከቢሮው ተቋማዊ አደረጃጀትና የስራ ሂደት ተሞክሮ እንዳገኙበትና በቢሯቸው ባሉ መዋቅሮች ተሞክሮውን ቀምረው ለማስፋፋት ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል። በተለይ ከቴክኖሎጂ ጋር በተያያዘ ያለው ለውጥ፣የሰራተኛው ውስጣዊ መነሳሳት, ትጋትና ቅንጅት ለብዙዎች ልምድ የሚሆን ነው ብለዋል።
ቢሮው አዲሱ የጥናት ሰነድ፣መመሪያዎች፣ ማንዋሎች፣ ቼክ ሊስቶችና ሌሎች መረጃዎች ተጠናክረው ቢቀጥሉ ሙልካም ነው የሚል ሀሳብ ሰጥተዋል።
በመጨረሻም ለልምድ ልውውጡ የመጣው ቡድኑ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮን አደረጃጀትና አሰራር በመዘዋወር ጎብኝቷል።