ማህበረሰብ ተኮር ውይይት

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

ማህበረሰብ ተኮር ውይይት

"የማህበረሰብ ውይይት ነዋሪው በየብሎኩ የሚፈጠረውን አለመግባባት በትንሽም በትልቅም በፍርድ ቤት ክርክር ጊዜና ገንዘቡን ሳይባክን እዛው በብሎኩ መፍታት የሚቻለውን በአቅማቸው መፍታት እንዲችሉ የሚያረግ ነው "

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ም/ቢሮ ሃላፊ አቶ ሚደቅሳ ከበደ

መጋቢት 11/2017 ዓ/ም(አዲስ አበባ )

** ** **

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ ለብሎክ አመቻቾች ማህበረሰብ ተኮር ውይይት ማንዋል እና የማመቻቸት ክህሎትን ማዳበር በሚል ርዕሰ ጉዳይ ሲሰጥ የነበረውን የአሰልጣኞች ስልጠና አጠናቋል ።

መድረኩ ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ም/ቢሮ ሃላፊ አቶ ሚደቅሳ ከበደ እንደተናገሩት የማሕበረሰብ አቀፍ ውይይት በብሎኩ የሚፈጠረውን አለመግባባት ማህበረሰቡ በትንሽም በትልቅም በፍርድ ቤት ክርክር ጊዜና ገንዘቡን ሳያባክን እዛው በብሎኩ መፍታት የሚቻለውን በአቅማቸው መፍታት እንድችሉ የሚያረግ ነው ብለዋል።

ከዚህም በተጨማሪ ህገ-ወጥነትን ለመከላከልና የህዝቡን ጥያቄ በፍጥነት ለመመለስ የሚያስችል መሆኑንም ገልጸዋል።

የዚህ ውይይት ትልቁ ፋይዳው በጡንቻ እና በድብደባ ሳይሆን በሀሳብ የበላይነት፣በውይይት እና በምክክር የሚያምን ትውልድ ለማፍራት የሚረደ መሆኑን ጠቅሰዋል።

ከስልጠናው ቦሃላ የጠነከረና የተሻለ በመተሳሰብና በመደማመጥ የሞላ ብሎክ እንደሚፈጠር ይጠበቃል ብለዋል።

የስልጠና ሰነዱን የቀረቡት አቶ አብረሃም ዕንግዳወርቅና አቶ ውድነህ አቢ የሕዝብ አደረጃጀት ዘርፍ ባለሙያዎች ሲሆኑ ሰፊ ውይይትም ተካሂዶበታል።

የውይይት መድረኩን የመሩት አቶ ልቅናው ታርኩ የሕዝብ አደረጃጀት ዘርፍ ቡድን መሪ እና የዘርፉ ባለሙያ አቶ አብረሃም ዕንግዳወርቅ ሰልጠናው በህዝብና መንግስት መሃል መተማመንን ለማምጣት እና ቀልጣፋ አግልግሎት ለመስጠት የሚረዳ ነውና ስልጡን፣ ጠያቂ እና በስተሳሰብ ልዕልና የሚያምን ህብረተሰብ ለመፍጠርና በከተማው ላይ የመጣውን ሰላም ዘላቂ ለማድረግ ነው ብለዋል ።