ልምድ ልውውጥ አርባምንጭ ከተማ

image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

ልምድ ልውውጥ አርባምንጭ ከተማ

በአቶ ተስፋዬ ጫኔ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ም/ቢሮ ኃላፊ የተመራው የልዑካን ቡድን ለልምድ ልውውጥ አርባምንጭ ከተማ ገባ።

መጋቢት 12/2027 ዓ.ም(አርባምንጭ)

********

በአቶ ተስፋዬ ጫኔ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ም/ቢሮ ኃላፊ የተመራው የልዑካን ቡድን ለልምድ ልውውጥ ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አርባምንጭ ከተማ ገብቷል።

የልምድ ልውውጥ አርባምንጭ የአየር ማረፊያ ሲደርስ የተከበሩ አቶ በቀለ ሎኮማ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የፀጥታ መምሪያ ምቢሮ ኃላፊና የሰላም ግንባታና የብዝሃነት አያያዝ ዘርፍ ኃላፊ፣

የተከበሩ አቶ ቃፌ ቃፍሬ የጋሞ ዞን ፀጥታ መምሪያ ኃላፊ፣ኢኒስፔክተር ደበበ ዑንቶ የጋሞ ዞን ፖሊስ አዛዥ፣የተከበሩ አቶ ምሕሩቁ ተሰማ የጋሞ ዞን አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊና ሌሎችም የዞንና የከተማ አመራሮች፣የጋሞ አባቶች ደማቅ አቀባበል አድርገውለታል።

ለልምድ ልውውጥ የተጓዘው የልዑካን ቡድን

አቶ ተስፋዬ ጫኔ የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ም/ል ቢሮ ኃላፊን ጨምሮ ሌሎችም ምክትል የቢሮ ኃላፊዎች፣አማካሪ፣የጽቤት ኃላፊ፣ ዳይሬክተሮች፣ቡድን መሪና ባለሙያዎች የተካተቱበት 12 አባላትን ያቀፈ ነው።

ለልዑካን ቡድኑ ማምሻውን አርባምንጭ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት አዳራሽ የጋሞ አባቶች የእርቅና የሽምግልና ሥነ-ሥርዓት 'ድቡሻ " ን በተመለከተ ገለፃ የተደረገለት ሲሆን በዚህ ወቅት የአርባምንጭ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ የተከበሩ ዶ/ር መስፍን ማንዛ፣የተከበሩ አቶ በቀለ ሎኮማ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የፀጥታ መምሪያ ም/ቢሮ ኃላፊ፣የተከበሩ አቶ ቃፌ ቃፍሬ የጋሞ ዞን ፀጥታ መምሪያ ኃላፊ በየተራ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር አድርገዋል።

ኃላፊዎቹ በንግግራቸውም:-

32 ብሔር ብሔረሰቦች ተከባብረውና ተቻችለው ወደሚኖሩባት የደቡብ ክልል አስተዳደር

እንኳን በሰላም መጣችሁ!

የግጭትና የፀብ እሳትን በእርጥብ ሳር ወደሚያጠፉት የጋሞ አባቶች ክልል እንኳን በሰላም መጣችሁ!

በመልክዓ ምድራዊ አቀማመጧና በተፈጥሮ ለምነቷ እንዲሁም የዓለም የቱሪስቶች የስበት ማዕከል ወደሆነችው አርባምንጭ ከተማ እንኳን በሰላም መጣችሁ! ብለዋል።

የልዑካን ቡድኑ በነገው ዕለት የመስክ ጉብኝት የሚያደርግ ሲሆን ተከታታይ መረጃዎችን የምናደርስ ይሆናል።