ሁለት ወራት ውስጥ በሰላም ጸጥታ አጠባበቅና ደህ...

image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

ሁለት ወራት ውስጥ በሰላም ጸጥታ አጠባበቅና ደህንነት ዙሪያ የተሰሩ ስራዎችን በተመለከተ ውይይት

ባለፈው 2 ወራት በከተማው ላይ ህግን በማስከበርና ወንጀልን በመከላከል ዙሪያ አመርቂ ውጤት መመዝገብ መቻሉ ተገለፀ ።

መጋቢት 23/2017 ዓ/ም(አዲስ አበባ )

** **

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ በተያዘው የ2017 አ. መረ ሁለት ወራት ውስጥ በሰላም ጸጥታ አጠባበቅና ደህንነት ዙሪያ የተሰሩ ስራዎችን በተመለከተ ውይይት አድርጓል ።

በውይይት መድረኩ ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ሀላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ እንዳሉት ከተማውን የጸጥታ ሁኔታ አስተማማኝ በማድረግ በኩል ከባለድርሻ አካላት፣ህዝቡንም የሰላም ባለቤት በማድረግና ለጸጥታውም አጋዥ እንዲሆኑ በማድረግ በኩል በተሰራው ስራ ዘላቂ ሰላምን ማምጣት ተችሏል ብለዋል

የሰላም ሰራዊት አባላትን በየግዜው በመልመልና፣በማሰልጠንና በማሰማራት፣ በተጨማሪም ማህበረሰብ ተኮር ውይይቶችን በማጠናከር ህብረ ብሔራዊ አንድነትና እሴቶች ዘላቂነት እንዲኖራቸው ማድረግና ግጭቶች ሲፈጠሩ በአካባቢያቸው ላይ መፍትሔ እንዲወስዱም ማድረግ መቻሉም ጠቁመዋል ።

በከተማዋ ላይ የተከናወኑት ትላልቅ የአደባባይ በዓላትና ኮንፈረንሶችም በታለመላቸው ልክ በሰላም መጠናቀቅ መቻላቸውን አስታውሰዋል

ቅንጅታዊ ስራዎችን በተመለከተ ከአጎራባች የሸገር ሲቲ ጋር በመስራት ህብረተሰቡ በሰላም ወጥቶ እንዲገባ የተጀመሩ የልማት ስራዎች ወቅቱን ጠብቀው እንዲጠናቀቁ እዛም እዚህም አልፎ አልፎ የሚታዩ የጸረ ሽብር ሴራዎችን የማክሸፍ፣ የጸጉረ ልውጥ እንቅስቃሴዎችን የመቆጣጠር፣ ህገ ወጥ የንግድና ኮንትሮባንዶችን የመከላከልና የመቆጣጠር በሀይማኖት ሽፍን የከተማውን ሰላም ለማወክ የሚጥሩ ኃይሎችን ሴራ የማክሸፍ ወዘተ.... ስራዎች መሰራታቸውንም ጠቅሰው በቀጣይ የተገኘውን ዘላቂ ሰላም አጠንክሮ መቀጠል እንደሚገባ አሳስበዋል ።

የቢሮው የጸጥታ ኦፕሬሽን ዘርፍ ም/ቢሮ ሀላፊ አቶ ተስፋዬ ደንድር በሁለት ወራት ውስጥ የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራትን በተመለከተ እንዲሁም የቢሮው የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ ም/ቢሮ ሀላፊ አቶ ሚደቅሳ ከበደ በጫኝና አውራጅ ማህበራት የዳሰሳ ጥናት ግኝትን በተመለከተ ሰነድ አቅርበው ሰፊ ውይይት ተደርጓል ።

በውይይት መድረኩ ላይ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ሀላፊ የቢሮው ም/ቢሮ ሀላፊዎች አማካሪዎች፣የጽህፈት ቤት ሀላፊ፣የሁሉም ክ/ከተማና ወረዳ የሰላምና ጸጥታ ጽ/ቤት ሀላፊዎች ተገኝተዋል።