




ግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና
በጫኝና አውራጅ ማህበራት አግልግሎት አሰጣጥ እንስፔክሸን ግኝት ላይ እና በስነ-ምግባርና ሙስና መከላከል ዙሪያ ግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና ተሰጠ።
መጋቢት 25/2017ዓ.ም ( አዲስ አበባ )
******
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ በጫኝና አውራጅ ማህበራት አግልግሎት አሰጣጥ እንስፔክሸን ግኝት ላይ እና በስነም-ግባርና ሙስና መከላከል ዙሪያ በአምስት ክላስተር ስልጠና ተሰጥቷል።
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ መሰብሰቢያ አዳራሽ በተካሔደው መድረክ ላይ በመገኘት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የቢሮ የአደረጃጀት ዘርፍ ም/ቢሮ ሃላፊ አቶ ሚደክሳ ከበደ ማህበራቱ ለማህበረሰቡ እፎይታ በመስጠት በከተማ ደረጃ ለውጥ ያመጡ መሆናቸውን ጠቅሰው ቢሮው 875 የሚሆኑ ማህበራትን መልሶ በማደራጀት መብትና ግዴታቸውን አውቀው በወጣው መመሪያ መሠረት እንዲሰሩ በየደረጃው በርካታ ስልጠናዎች መሰጠታቸውን፣ እንዲሁም የስነ-ምግባር ጉድለት ያለባቸውንና ከመመሪያ ውጪ የሚሰሩ ማህበራት ኢንዲታረሙ የማድረግ ስራመስራቱን ገልጸዋል።
ከማህበረሰቡ ጋር በመግባባት በትህትና እና በመተሳሰብ ማገለገል፣ ባላቸው አቅም ማዕድ ማጋራት፣ አቅመ ደካማዎችን መርዳትና የሰላምና ፀጥታ ስራዎችን የሚያግዙ ማህበራት ማፍራት ተችሏል ከሉ በኋላ ስልጠናው ጥሩ የሰሩ እንዲበረታቱ እና መመሪያውን ተግባራዊ ሳያደርጉ ህዝቡን የሚያስቸግሩ ካሉም ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ለማስገንዘብ ነው ብለዋል።
በአምስቱም ክላስተር የግንዛቤ ማስጨበጫ ሰነድ ፤ የጫኝና አውራጅ ማህበራትን ለመከታተል የወጣ ደንብና መመርያን፣ተከትሎ እየሰሩ መሆኑ ከክፍለ ከተማ እስከ ወረዳ በተደረገ ዳሰሳ የተገኘው ውጤት፣ ጥንካሬ እና ክፍተቶች በዘርፉ ዳይረክቶሬት ዳይረክተር እና ባለሙያዎች ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።