በመልካም አስተዳደር ዘጠኝ ወራት ውስጥ የተሰሩ ስራዎች ግምገማ
የቢሮው የለውጥና መልካም አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በዘጠኝ ወራት ውስጥ የተሰሩ ስራዎችን ገመገመ።
መጋቢት 25/2017 ዓ/ም(አዲስ አበባ )
******
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የለውጥና የመልካም አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በዘጠኝ ወራት ውስጥ የተከወኑ ዋና ዋና ስራዎችን በተመለከተ በጋራ ገምግሟል።
በግምገማው መድረክ ላይ በመገኘት መልዕክት ያስተላለፉት የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ አማካሪ አቶ ገብሬ ዳኘው እንዳሉት የመልካም አስተዳደርና የከተማው ህብረተሰብ ችግሮች የነበሩ ዘጠኝ ጉዳዮች የተፈቱ እንዲሁም ሶስቱ ደግሞ በሒደት ላይ እንዳሉ ተናግረዋል።
ይህም ውጤት ሊመጣ የቻለውም በጋራ በመሰራቱ እንደሆነ ኃፊው በመግለፅ ችግሮችና ቅሬታዎች ሲኖሩ በወቅቱ መፍታት ካልተቻለ ወደ ግጭት ስለሚያመሩ ልዩ ትኩረት መስጠት እንደሚገባ አሳስበዋል።
በውይይቱ ላይ የተገኙት የሁሉም ክ/ከተማ የለውጥና መልካም አስተዳደር አስተባባሪዎቹ እንዳሉትም በተለያዩ ግዜ የሚነሱ የመልካም አስተዳደር ችግሮች እንደየክ/ከተሞቻቸው ተጨባጭ ሁኔታ በመፈታት ላይ መሆናቸውን
ገልፀዋል።
በውይይቱ ላይ አቶ ገብሬ ዳኘውን ጨምሮ የማዕከልና የሁሉም ክ/ከተማ የለውጥና
የመልካም አስተዳደር ሰራተኞችና አስተባባሪዎች ተገኝተዋል ።