



የሰላም ዕሴት ግንባታ ዘርፍ የዘጠኝ ወራት እቅድ አፈጻጻም
የ2017 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት እቅድ አፈጻጻም ተገመገመ
መጋቢት 26/2017 ዓ/ም(አዲስ አበባ )
******
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የሃይማኖትና ሰላም ዕሴት ግንባታ ዘርፍ ከክ/ከተማ እስከ ወረዳ ከሚገኙ አስተባባሪዎችና ቡድን መሪዎች ጋር የበጀት ዓመቱ የዘጠኝ ወራት እቅድ አፈጻጻም ገምግሟል።
መድረኩ ላይ ተገኝተው መክፈቻ ንግግር ያደረጉት አቶ ተስፋዬ ጫኔ የቢሮው ም/ል ኃላፊ በዘጠኝ ወራት ውስጥ ታቅደው የተከናወኑ፣
ጠንካራና ደካማ ጎኖችን በመገምገም የታዩ ክፍተቶችን በጥረት በመሙላት በዓመቱ መጨረሻ የላቀ አፈፃፀም ላይ ለመድረስ ነው ብለዋል።
የዘጠኝ ወራት እቅድ አፈጻጻም ሪፖርት ያቀረቡት የዘርፉ ባለሙያ አቶ ኤልያስ ቀጄላ ሲሆኑ የሪፓርቱ አላማ፣በ9ወራት የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት፣ ጠንካራ ጎኖች እና ደካማ ጎኖች፣ ያጋጠሙ ችግሮችና የተወሰዱ መፍትሔዎችን በዝርዝር አብራርተዋል።
በሪፖርቱም የተለያዩ ሃይማኖታዊና ባህላዊ የአደባባይ በዓላት እንዲሁም አህጉር አቀፍ እና አገር አቀፍ ታላላቅ ስብሰባዎችና ኮንፈረንሶች በሰላም ተመከብራቸውና ሙካሄዳቸው፤ የሃይማኖት ተቋማት በውስጣቸው ያለውን የመልካም አስተዳደር ችግሮች በራሳቸው እንዲፈቱ ማድረግ እና በእነሱ አቅም ያልተቻለውን መንግስት መፍታት መቻሉ ከተጠቀሱት ጠንካራ ጎኖች ውስጥ ተጠቃሽ ናቸው።
በውይይቱ ማጠቃለያ ላይ አቶ ተስፋዬ እንደተናገሩት በቀሪ ወራት የዘርፉን ዕቅዶች በተሟላ ሁኔታ መፈፀም ይገባል ካሉ በኃላ ችግሮችን በሃላፊነት ብቻ ሳይሆን በሰብዓዊነት ለመፍታት መሞከርም ተገቢ እንደሆኑ አሳስበዋል።