ለቢሮው ሰራተኞች በመንግስት ሰራተኞች ደንብ ቁጥ...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

ለቢሮው ሰራተኞች በመንግስት ሰራተኞች ደንብ ቁጥር 179/2017 ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ።

ለቢሮው ሰራተኞች በመንግስት ሰራተኞች ደንብ ቁጥር 179/2017 ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ።

መጋቢት 26/ 7/2017 ዓ/ም(አዲስ አበባ )

******

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የሰው ሀብት ዳይሬክቶሬት በመንግስት መስሪያ ቤቶችና የሰው ኃይል ስምሪት በልዩ ሁኔታ ለማመጣጠን በወጣው መመሪያ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል።

ስልጠናው የሰጡት የአዲስ አበባ አበባ ከተማ የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ የክትትልና ድጋፍ ባለሙያ አቶ መላኩ ተመስገን ሲሆኑ በስልጠናው ወቅት እንዳሉት የምጥጥኑ አስፈላጊነት በከተማ ደረጃ የአፈፃፀም ክፍተት እና የመልካም አስተዳደር ችግር ለመቅረፍ ብሎም ተቋማት ተልዕኳቸውን በተገቢው መንገድ እንዲያሳኩ ለማድረግ ነው ብለዋል።

ጥራት ያለው፣ ቀልጣፋ፣የአገልግሎት አሰጣጥ ስርዓትን ከማስፈንም በተጨማሪ አንዳንድ ተቋማት የሰው ሀይሉ ከፍተኛ በመሆኑ በማዕከል ደረጃ ስራንና ሰራተኛን በማገናኘት ውጤታማነትን ማሳደግ ከማስፈለጉ ባሻገር የተገልጋይን እርካታ ከፍ ለማድረግ እንደሆነም ጭምር አቶ መላኩ ተናግረዋል።