


የቢሮ ምዘና
ከዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ጽቤት፣ከፕላን ኮሚሽንና ከፐብሊክ ሰርቪና ሰው ኃብት ልማት ቢሮ የተውጣጣ ቡድን በአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ምዘና አካሄደ።
መጋቢት2017/2017 ዓ.ም( አዲስ አበባ )
********
ከዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ጽቤት፣ከፕላን
ኮሚሽንና ከፐብሊክ ሰርቪና ሰው ኃብት ልማት ቢሮ የተውጣጣ ቡድን በአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የ2017 ዓ.ም የስድስት ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ምዘና አካሂዷል።
ምዘናው የቢሮውን የሁሉንም ዘርፎች ዕቅድ አፈፃፀም ደረጃ ለማወቅ በጥልቀት የተካሄደ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።
በምዘናው ማጠቃለያ ወቅት እንደተገለፀው የቢሮው የለፉት ስድስት ወራት የዕቅድ አፈፃፀም በተሻለ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ በቡድኑ የተገለፀ ሲሆን በቀጣይ ቢስተካከሉ ያሉዋቸውንም ጥቃቅን አሠራሮች ላይ አስተያየት ሰጥተዋል።
በምዘናው ማጠቃለያ ውይይት ላይ የቢሮው ኃላፊ ክብርት ወሮ ሊዲያ ግርማ፣ ም/ል ቢሮ ኃላፊዎች አማካሪ፣የጽቤት ኃላፊ፣ደይሬክተሮችና መዛኝ የቡድን አባላት ተገኝተዋል።