



የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ የዘጠኝ ወራት የዕቅድ አፈጻጸሙን ገመገመ
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ የዘጠኝ ወራት የዕቅድ አፈጻጸሙን ገመገመ
ሚያዝያ 1/2017ዓ.ም (አአሰፀአቢሮ)
*****
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ የዘጠኝ ወራት የዕቅድ አፈጻጸሙን ገምግሟል።
በግምገማዊ ውይይቱ ላይ የአዲስ አበባ የከተማሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ሚደቅሳ ከበደን ጨምሮ ዳይሬክተሮች፣ቡድን መሪዎችና ባለሙያዎች ተገኝተዋል።
የአዲስ አበባ የከተማ አስተዳደር በህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ሚደቅሳ ከበደ እንደተናገሩት ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ህዝቡን የሰላም ባለቤት ለማድረግ፣ ህዝባዊ መድረኮች በማመቻቸት፣ የሰላም ሰራዊትን በማጠናከርና ከፀጥታ አካላት ጋር በማቀናጀት ውጤታማ ተግባራት ተከናውነዋል።
በተጨማሪም በከተማችን ዓለም አቀፍ፣አህጉር አቀፍና አገር አቀፍ ታላላቅ ኮንፈረንሶችና ጉባኤዎች ሰላማዊ እንዲሆኑ፣ የአደባባይ በዓላት በሰላም በፍቅርና በአንድነት እንዲከበሩ በዘጠኝ ወራት አፈጻጸም ስኬት ተመዝግቧል።
አቶ ሚደቅሳ አክለውም በመረጃ አያያዝና ፍሰት እንዲሁም ጥራት መሻሻል እንዲሚገባ አንስተው በቀጣይ የተሳካ ህዝባዊ ውይይትን በመዘርጋት አመራሮችና ባለሙያዎች ቁርጠኛ ሊሆኑ ይገባል።
የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ ዳይሬክተር ወይዘሮ ፍሬህይወት በለጠ በበኩላቸው በቀሪ ወራት የሚከናወኑ ስራዎች ችግር ፈቺና ውጤታማ ሆነው ወቅቱን ጠብቀው በሪፖርት ሊቀርቡ ይገባል ሲሉ ተናግረዋል።
የህዝብ አደረጃጀትና የብዙሀን ማህበራት ቡድን መሪ በሆኑት በአቶ ልቅናው ታሪኩ የዘጠኝ ወራት የዕቅድ የአፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ በተሳታፊዎች ሀሳብና አስተያየት ተሰጥቶበታል።
በመጨረሻም በቀሪ ወራት የሚከናወን የስራ አቅጣጫ በመስጠት የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማዊ ውይይቱ ተጠናቋል።