የሀብት ማሳወቅና ማስመዝገብ ስርዓት

image description
image description
image description
image description
- recent news   

የሀብት ማሳወቅና ማስመዝገብ ስርዓት

የሀብት፣ ጥቅም፣ ማሳወቅና ማስመዝገብ ስርዓትን አስመልክቶ ስልጠና ተሰጠ።

ሚያዝያ 2/2017 (አአሰፀአቢሮ)

*******

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ስነ-ምግባርና የፀረ-ሙስና መከታተያ ዳይሬክቶሬት ከአዲስ አበባ ከተማ ስነ-ምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ጋር በመተባበር ለሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የማዕከል ሰራተኞች የሀብት፣ ጥቅም፣ ማሳወቅና ማስመዝገብ ስርዓትን አስመልክቶ ስልጠናው ሰጥቷል።

ሥልጠናውን የሰጡት አቶ አቤል ሳኩሜ የአዲስ አበባ ከተማ ስነ-ምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን የስልጠና ባለሙያ ሲሆኑ የስልጠናው አላማ በግብረ-ግብነት፣ በሞራል እሴት በስነ-ምግባር የታነፀ ዜጋ በመፍጠር፤ ማህበረሰባዊ ደንቦችን በማክበርና በማሳደግ እንዲሁም የሀብት ምዝገባን ባህል ለማድረግ ያለመ ነው ብለዋል።

የሀብት ምዝገባ ሙስናን ለመከላከል፣

ግልፀኝነትን ለመፍጠር፣ የጥቅም ግጭትን ለመቆጣጠር፣ህዝባዊ ተጠያቂነትን ለማረጋገጥና እንዲሁም የመልካም አስተዳደርን ለማስፈን እንደሚያግዝ በስልጠናው ላይ ተብራርቷል።

በስልጠናው ተሳታፊዎች ጥያቄ ሀሳብና አስተያየት በመስጠት በተጨማሪም ለውጤታማነቱ በትኩረት እንደሚሰሩ ገልፀዋል ።