በጨለማ የተዋጡ እና ወንጀል ሲፈፀምባቸው የነበሩ...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

በጨለማ የተዋጡ እና ወንጀል ሲፈፀምባቸው የነበሩ ስፍራዎችን መብራት

"ጨለማን ተገን ተደርገዉ የሚፈፀሙ ወንጀሎች ለመቀነስ የተሰራዉ ስራ አበረታች ነው”

ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ

ሚያዝያ 16/2017 ዓም(አአሰፀአቢሮ )

******

ከዚህ ቀደም በጨለማ የተዋጡ እና ወንጀል ሲፈፀምባቸው የነበሩ ስፍራዎችን በማህበረሰቡ ተሳትፎ፣ በአዲስ አበባ ከተማ የመብራት አስተዳደር ባለስልጣንና እና በአመራሩ ቅንጅት በብርሀን የተሞሉ እና ጨለማን ተገን በማድረግ የሚፈፀሙ ወንጀሎች እንዲቀንሱ በማድረግ አስተማማኝ ሰላም የሰፈነባቸው ስፍራዎች ማድረግ መቻሉን አዲስ አበባ ከተማ የሰላም እና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ ገለፁ።

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላም እና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የማዕከልና የክፍለ ከተማ አመራሮች፣ ከከተማ እስከ ክ/ከተማ ያሉ የመብራት አስበሪ ኮሚቴ አመራሮችና ሌሎቸ‍እ የሚመለከታቸዉ አካላት በጉለሌ ክፍለ ከተማ ጨለማ ቦታን ወደ ብርሀን የቀየሩ ሞዴል ብሎኮችና ቀጠናዎች የመስክ ምልከታ አድርገዋል፡፡

በምልከታው የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ እንደተናገሩት በጉለሌ ክፍለ ከተማ ጨለማ በመሆናቸዉ ምክንያት ለተለያዩ ወንጀሎች ተጋላጭ የነበሩ አካባቢዎችን ወደ ብርሀን በመቀየር ሞዴል የማድረግ ስራዎችን በመስራት ለነዋሪው ምቹ አካባቢ በመፍጠር ወንጀልን ለመከላከል የተከናወኑ ተግባራት የሚደነቁ ናቸው ብለዋል። ይሄም በመሆኑ ምክንያት ጨለማን ተገን ተደርገዉ ሲፈፀሙ የነበሩ ንጥቂያዎች፣ ዘረፋዎች፣ ሀንግ ማድረጎች፣ ፆታዊ ትንኮሳዎች፣ ግድያዎችና መሰል ወንጀሎች መቀነስ ተችሏል ብሏል። ቢሮ ሀላፊዋ ጨለማ ብሎኮችና ቀጠናዎች መብራት እንዲያገኙ ላደረጉ አካላት በሙሉ ምስጋና ችሯል።

በመሆኑም በጉለሌ ክ/ከተማ በተለያዪ ብሎኮችና ቀጠናዎች ያየነዉ ምርጥ ልምድና ተግባር ወደ ሌሎች ብሎኮች፣ ቀጠናዎች፣ ወረዳዎችና ክፍለ ከተሞች በማስፋት የከተማችንን ሰላምና ጸጥታ በአስተማማኝ መሠረት ላይ መገንባት ይገባናል ብለዋል፡፡

የጉለሌ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ወልዴ ወገሴ በበኩላቸው እንደተናገሩት በክ/ከተማችን ከዚህ ቀደም ጨለማ በነበሩ በነበሩ ብሎኮችና ቀጠናዎች በርካታ ዘረፋዎች፣ ንጥቂያዎች፣ ከመሸ በሀኀላ በነፃነት የመንቀሳቀስ ስጋቶች፣ አልፎ አልፎ ደግሞ በስለት ወግቶ የመግደል ሙከራዎች እንደነበሩ አዉስተዉ አሁን ደግሞ በአመራሩ አስተባአሪነት፣ በመብራት ባለስልጣን ተግባሪነት፣ በህዝቡ ቀጥተኛ ተሳትፎና ባለቤትነት ጨለማ የነበሩ የነበሩ ሰፈሮች ወደ ብርሀን በመቀየራቸዉ ከዚህ በፊት ሲፈፀሙ የነበሩ ወንጀሎች መቀነሳቸዉን አበክረዉ አንስተዋል።

አክለውም ዛሬ በተለያዩ ወረዳዎች የታዩ ለውጦችን በማስቀጠል ጉለሌን የሰላምና የብልጽግና ተምሳሌት እንድትሆን እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።

ጨለማ ብሎኮችና ቀጠናዎች ወደ ብርሀን እንዲቀየሩ በማድረግ የማህበረሰቡ የወንጀል ስጋት እንዲቀንስ ላደረጉ አካላት በሙሉ ምስጋና አቅርበዋል።

አመራሮቹ ከምልከታዉ ጎን ለጎን በስምሪት ላይ የነበሩ የሰላም ሰራዊት፣ የደንብ ማስከበርና የአዲስ አበባ ፓሊስ አባላት የማበረታታት ስራ ሰርቷል።

ከመስክ ምልከታው በኋላም በአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ሀላፊ መሪነት የዉስጥ ለዉስጥ የበር ደጃፍና የመንገድ ዳር መብራት የማስበራት ስራ አፈፃፀም ሪፖርት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ህ/ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ቢሮና በአዲስ አበባ ከተማ መብራት አስተዳደር ባለስልጣን አመራሮች አማካኝነት ሪፖርት ቀርቦ በቀጣይ በርብርብ መሰራት ያለባቸዉ ስራዎች ላይ የቢሮ ሀላፊዋ ጥብቅ አቅጣጫዎች በማስቀመጥ መድረኩ ተቋጭቷል።

በጉብኝቱ ላይ የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ፣ የ11ዱም ክፍለ ከተማ የሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊዎች፣ የህ/ሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ፅ/ቤት ሀላፊዎች፣ ስራ አስኪያጆች፣ የማ/ሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት ዲቪዥን ሀላፊዎች፣ የጉለሌ ክ/ከተማ አመራሮች ፣ የጸጥታ አካላት ፣ የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኃላፊዎችና ኦፊሰሮች ፣ የሰላም ሰራዊት አባላት ተገኝተዋል።