




ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ እና የደንብ ማስከበር ባለስልጣን በጋራ የዘጠኝ ወር የ2017 አፈጻጸማቸውን ገምግመዋል።
አዲስ አበባ የህግ የበላይነት የተረጋገጠባት ከተማ እንድትሆን ለማድረግ በቅንጅት በመስራት በዘጠኝ ወራቱ አበረታች ውጤት ተመዝግቧል።
• ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳር ቢሮ ኃላፊ
ሚያዚያ 18/2017(አአ ሰፀአ ቢሮ)
*****
ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ እና የደንብ ማስከበር ባለስልጣን በጋራ የዘጠኝ ወር የ2017 አፈጻጸማቸውን ገምግመዋል።
የተቋማቱ የ2017 የስራ በጀት ዓመት የዘጠኝ ወር አፈጻጸም በዝርዝር ቀርቦ ሀሳብና አስተያየት ተሰጥቶታል።
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወይዘሮ ሊዲያ ግርማ በመክፈቻ ንግግራቸው እንደገለፁት በከተማዋ የተመዘገበው ልማትና ሰላም ዘላቂ ለማድረግ ነዋሪዎች በሰላም ወጥተው እንዲገቡ ዘርፈ ብዙ ተግባራት ተከናውነዋል።
በተጨማሪም ከተማዋ ህብረ-ብሔራዊነቷን ይዛ እንድትቀጥል፤ ስለ ሀገር ወዳድነት፤ ሀገረ መንግስት ግንባታ የተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ስልጠና ተሰጥቶ ከህብረተሰቡ ጋር የጋራ ግንዛቤ ለመያዝ ተችሏል።
የሰላም ሰራዊት አባላት መልምሎ አሰልጥኖ ወደ ስራ በማሰማራት አካባቢያቸውን እንዲጠብቁ በማድረግ ትልቅ ስራ ተሰርቷል ብለዋል።
ቢሮ ኃላፊዋ አክለውም አዲስ አበባ የህግ የበላይነት የተረጋገጠባት ከተማ እንድትሆን ለማድረግ በቅንጅት በመስራት በዘጠኝ ወራቱ አበረታች ውጤት ተመዝግቧል ብለዋል።
በከተማዋ በ7/24 የስራ ባህል የፀጥታና የደህንነት ችግሮች እንዳይፈጠሩ የአደባባይ ሁነቶች ሰላም እንዲሆኑ ከሰላም ወዳዱ ህዝብ ጋር በመሆን በቅንጅት በመስራት በአመለካከትና በእውቀት የተሻለ አመራርና ባለሙያ በማሰማራት ውጤታማ ተግባራት ተከናውነዋል።
በተጨማሪም ከተማዋ ህብረ-ብሔራዊነቷን ይዛ እንድትቀጥል፤ ስለ ሀገር ወዳድነትና ሀገረ መንግስት ግንባታ የተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ስልጠና ተሰጥቶ ከህብረተሰቡ ጋር የጋራ ግንዛቤ ለመያዝ ተችሏል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ በበኩላቸው የህዝቡን ተሳትፎ በማሳደግ፣ የአመራርና ባለሙያዎችን ቅንጅታዊ አሰራር በማጠናከር በዘጠኝ ወራት የስራ አፈጻጸም ተጨባጭ ለውጥ መጥቷል ብለዋል።
ሻለቃ ዘሪሁን አክለውም ህብረታችንና ትብራችንን በማሳደግ ለህገወጦችና አጭበርባሪዎች በር በመዝጋት በ2017 የታቀዱ ቁጥሮች ከነባራዊ ሁኔታው ጋር በማዛመድ ውጤታማ ሆነናል ሲሉ ተናግረዋል።
በግምገማው ላይም የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ክብርት ወ/ሮ ሊድያ ግርማ እና ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅን ጨምሮ ከማዕከል እስከ ወረዳ የሚገኙ የሁለቱ ተቋማት የስራ ኃላፊዎች፣ ዳይሬክተሮች እንዲሁም አስተባባሪዎችና ቡድን መሪዎች ተገኝተዋል።