





የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና
ፌደራሊዝምና የብዝሃነት አያያዝ በኢትዮጵያ በሚል ርዕሰ ጉዳይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ ።
ግንቦት 4/2017 ዓ.ም (አአ ሰፀአ ቢሮ)
*****
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የሀይማኖት እና ሰላም እሴት ግንባታ ዘርፍ "ፌደራሊዝምና የብዝሃነት አያያዝ በኢትዮጵያ ተግዳሮቶችና መፍትኔ ሀሳቦች" በሚል ርዕሰ ጉዳይ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ለተወጣጡ ሴቶችና ወጣቶች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል።
በግንዛቤው ማስጨበጫ መድረኩ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት አቶ ተስፋዬ ጫኔ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ም/ቢሮ ሀላፊ እንዳሉት በአንድም በሌላ በኩል ስለ ፌደራሊዝም እንደምናውቅ የሚታወቅ ሲሆን በተለያዩ ግዜ ደግሞ ሀሳብን ማዳበር ተገቢ ስለሆነ የፌዴራሊዝም ስርዓትን ከሚከተሉ ሀገሮች አንዷ ኢትዮጵያ እንደ መሆኗ መጠን ህዝቡን መሰረት ያደረገ አተገባበር ትከተላለችም በማለት ሀሳባቸውን ገልፀው
ብዝሀነት ያለበት ሀገር ውስጥ የተጠናከረና በተገቢው መንገድ የተገነባ የሀገር ግንባታ እንዳለም በመጠቆም ስርአቱም እየተተገበረ ይገኛል ያሉት ሀላፊው እንደ ሀገር ሥርዓቱን ተግባራዊ በማድረግ ሂደት ውስጥ የምናተርፈው ዘርፍ ብዙ ጠቀሜታም ስላለው እሱን በተገቢው መንገድ በመተግበር ለጋራ ሀገር በጋራ መስራትም ይገባል ሲሉ ተናግረዋል።
የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናውን መነሻ ሰነድ ያቀረቡት ወ/ሮ አዲስ አለም ዘነበ የሀይማኖት እና ሰላም እሴት ግንባታ ዘርፍ የስልጠና ቡድን መሪ እንዳሉትም ከሀገራዊ ፍላጎት በመነሳት አንድ በሚያደርገን ጉዳይ ላይ በተለያዩ ሰው ተኮር ተግባራት ላይ በታማኝነት በመሰማራት ለመጪው ትውልድ የሚተርፍ ስራን መስራት ይገባልም ህብረትን በማጠናከርና ከማንነትና ከብሔርተኝነት በተጨማሪም ከጽንፈኝነት የጸዳ የፌደራሊዝም ግንባታን ማጠናከር ይገባል በማለት በሰነዱ ላይ ጠቅሰዋል ።
አቶ ኤልያስ ቀዴላ የቢሮው የሀይማኖት እና ሰላም እሴት ግንባታ ዘርፍ የስልጠና ቡድን መሪ በበኩላቸው እንዳሉት አልፎ አልፎ የሚስተዋሉ የተሳሳቱ እሳቤዎችን በማረምና ብዝሃነትን በማጠናከር እንደ ዜጋ ሰላምን በማምጣት ጥረት ውስጥ የበኩላችንን ሚና ልንወጣ ይገባል በማለት ተናግረዋል።
በስልጠናው ላይ አቶ ተስፋዬ ጫኔ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ም/ቢሮ ሀላፊ፣የሁሉም ክ/ከተማ የዘርፉ አስተባባሪዎችና ቡድን መሪዎች እንዲሁም
ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተወጣጡ ሴቶችና ወጣቶች ተገኝተዋል ።