







ቢሮው በዘጠኝ ወራት የመልካም አስተዳደርና በአገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ ውይይት አደረገ።
ቢሮው በዘጠኝ ወራት የመልካም አስተዳደርና በአገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ ውይይት አደረገ።
ግንቦት 5 /2017 (አአ ሰፀአ ቢሮ )
******
የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ በዘጠኝ ወራት የመልካም አስተዳደርና በአገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ ውይይት አድርጓል።
በዘጠኝ ወራት የተከናወኑ የአገልግሎት አሰጣጥና የመልካም አስተዳደር ተግባራትን አስመልክቶ ዝርዝር ሪፖርት በቢሮው አማካሪው አቶ ገብሬ ዳኘው ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል።
የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የአደረጃጀት ዘርፍ ም/ ኃላፊ አቶ ሚዴክሳ ከበደ እንደተናገሩት ቢሮው ህዝብን ዝቅ ብሎ በማገልገል፣ ሰላምን በማስፈን፣ሁነቶችን በሰላም በማክበር፣ አዋኪ ድርጊቶችን በመከላከልና ህገ-ወጥ የምርት ስወራን በማስቀረት ዘርፈ-ብዙ ተግባራት ተከናውነዋል።
አቶ ሚደቅሳ አክለውም ከህብረተሰቡ ጋር በመቀራረብ ችግሮችን ከመሰረቱ በመለየት በዘጠኝ ወራት አበረታች ተግባራት መከናወናቸውን አንስተዋል።
የቢሮው የሰላም እሴት ግንባታ ዘርፍ ምክትል ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ጫኔ በበኩላቸው የከተማውን ሰላምና ደህንነት በማረጋገጥ ህብረተሰቡ ትልቅ ሚና እንዳለው ጠቅሰው በተቀናጀ አሰራር ችግሮችን እየፈታን ምቹና ሰላማዊ አካባቢን በመፍጠር ተቀራርበን እንሰራለን ሲሉ ተናግረዋል።
አቶ ተስፋዬ አክለውም ነዋሪዎች ለማህበራዊ ተቋማትና ለሚኖሩበት አካባቢ የሰላም ዋስትና መሆን አለባቸው ብለዋል።
የቢሮው አማካሪ አቶ ገብሬ ዳኘው እንደተናገሩት ህጋዊ የትራንስፖርት ስምሪት እንዲሰፍን፣ የማህበራዊ ተቋማትን ከአዋኪ ድርጊቶች በመጠበቅ፣ እንዲሁም ከፀጥታ ተቋማትና ከነዋሪው ጋር ተቀራርቦ በመስራት በዘጠኝ ወራቱ አመርቂ ውጤት ተመዝግቧል ሲሉ ተናግረዋል።
የቀጣይ ስራው አቅጣጫ በመስጠት የዕለቱ የውይይት መርሃግብር ተጠናቋል።
በውይይቱ ላይ የኃይማኖት አባቶች የሴትና የወጣት አደረጃጀቶች ተዋቂ ግለሰቦችና የብሎክ ተወካዮች ተገኝተዋል።